በቢሮው የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመቅረፍ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለፀ፡፡

መጋቢት 8/ 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የተከለሰ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል፡፡
በዛሬው ዕለት ቢሮው በበጀት ዓመቱ ባለፉት 7 ወራት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በመልካም አስተዳደርና ሌብነትና ብልሹ ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በመጋቢት ወር ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከቅርንጫፍ ስራ እስክጆችና ም/ስራአስክች ፣ የስራ ሂደት መሪዎች እንዲሁም ከማዕክል ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ የማጠቃለያ ሃሳብ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመቅረፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
ቢሮው ባለፉት 7 ወራት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመቅረፍ የዕቅድ ክለሳ ማድረጉን በማስታወስ በዚህም እየተገኙ ባሉ ለውጦች መዘናጋት እንደማይገባና ለላቀ ውጤታማነት ዕለት በዕለት መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ በየደረጃው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች አሁን የተገልጋዮች እንግልትና ቅሬታ መኖሩን የገለፁት አቶ ቢኒያም ችግሩን በተሟላ ደረጃ በመቅረፍ የግብር ከፋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ ሁሉም ቁርጠኛ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም በየደረጃው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ በቢሮው ተጠንተው ወደ ተግባር የተሸጋገሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር በማሸጋገር ግብር ከፋዮች ወደ ተቋሙ የሚመጡባቸውን ምክንያቶች መቀነስ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የመረጃ አያያዝና የጥራት ችግሮችን መቅረፍ፣ የግልጸኝነትና የተጠያቂነት አሰራርን በተሟላ ደረጃ ወደ ተግባር ማሸጋገር በልዩ ትኩረት ሊፈፀሙ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር፣ ምቹ የስራ አካባቢዎችን መፍጠር፣ የችግሩን ስፋና ጥልቀት በልኩ በመረዳት የመፍትሄ አካል ሆኖ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱረማን ባለፉት 7 ወራት በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የውይይት መነሻ ሃሳብ አቅርርበዋል፡፡
በመድረኩ የተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው ባለፉት 7 ወራት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች አበረታች ቢሆኑም አሁንም ግብር ከፋዮች የሚያነሷቸው ችግሮች በመኖራቸው ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረጉ ጥረቶች ኃላፊነታቸውን በመወጣት ረገድ ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *