የኢኮኖሚ ነፃነቷን በማረጋገጥ የበለፀገች ሀገር መገንባት የዚህ ትውልድ ተቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
የካቲት 09/2018 ዓ.ም የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች 130ኛው የአድዋ ድል ምክንያት በማድረግ ውይይት አካሄዱ፡፡ የአድዋ እሴት ለሁለንተናዊ ሃገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የድል በአል አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ የፅ/ቤት ኃላፊው አቶ አዳነ ሱሌ አድዋ ዘመን የማይሽረው በደማቅ የተጻፈ የድል ታሪክ፣ ጀግኖች አባቶቻችን ድንበር ተሻጋሪና ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ቀንዲል የሆኑበት፣ ለእኛ ኢትዮጲያውን…
