የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዕለታዊ ደረሰኝ ሳይዙ ጭነት በመጫን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 5 ተሽከርካሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ።

ነሀሴ 25/ 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ባካሄደው የቁጥጥር ስራ ዕለታዊ ደረሰኝ ሳይዙ ጭነት በመጫን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ ባሻገር ለጫኑት ዕቃ ደረሰኝ ማስቆረጡ ነው አሳውቋል። የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የህግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ብሩክታይት ባህሩ እንደገለፁልን…

Read More

በ2018 በጀት አመት ለመሠብሰብ የታቀደውን ገቢ ለማሳካትና የህግ ተገዢነት ስራን ለማጠናከር ወደ 24 የሚጠጉ አሰራሮችን ወደ ተግባር በማሸጋገር ተጨባጭ ውጤቶች እየታዩበት መሆኑ ተገለፀ ።

ነሐሴ 14 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት አመቱ የታቀደውን የከተማዋን ገቢ በአግባቡ ለመሠብሰብ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተግባር አስገብቶ እየሰራ ይገኛል ። ፍትሀዊ የሆነ የታክስ ( ግብር ) አሰባሰብ ስርዓት በከተማዋ ማስፈንና ይበልጥም የሚሰበሰበው ገቢ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን በህግ ተገዢነት ዘርፍ አሰራርን በመፈተሽ በማስተካከልና…

Read More

የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ባለሙያዎች ፈጣንና ጥራት ያለው መረጃ በአግባቡ በማደራጀትና ለተቋም አመራሮች በማቅረብ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲወሰን የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባቸው ተገለፀ፡፡

መስከረም 9 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቅርንጫፍ ፅ/ቤት የበጀትና ዕቅድ ክትትልና ድጋፍ የስራ ሂደቶችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የስልጠና መድረኩን የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በየደረጃው ያለው የእቅድ ክፍል ጥራት ያለው፣ ፈጣንና በአግባቡ የተደራጀና የተተነተነ መረጃ ለውሳኔ በማቅረብ የተቋሙ ዕቅድ እንዲሳካ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ከትክክለኛና…

Read More

ቢሮው የግብር አሰባሰብ ስርዓቱ ፍትሃዊ ለማድረግና ለሌብነትና ብልሹ አሰራር በር የከፈቱና ለውሳኔ አሰጣጥ አሻሚ የሆኑ ጉዳዮች ለመቅረፍ 24 አዳዲስ አሰራሮች በመዘርጋት ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ተገለፀ፡፡

ነሐሴ 28 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አጥንቶ ወደ ተግባር ባሸጋገራቸው 24 አሰራሮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫው የቢሮው የታክስ ውሳኔ ቅሬታ ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ ደጌ ቢሮው ግብር ከፋዮች በተለያዩ ጊዜያት የሚያነሷቸው የመልካም አስተዳደር፣ የሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመዝጋት በየጊዜው የማሻሻያ አሰራሮችን ለግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ…

Read More

ለግንዛቤዎት

የግብር ከፋዩን የሂሳብ መዝገብ የሚያዘጋጁ የሂሳብ አዋቂዎች እና የውጪ ኦዲተሮች ኃላፊነት እና ሚና • የሂሳብ ባለሙያው የግብር ከፋዩ አመታዊ ግብር ለማሳወቅም ሆነ ለመደበኛ የኦዲት ስራ የሚያዘጋጀው የሂሳብ መዝገብ በቢሮው በተዘጋጀው የአሰራር ሰነድ ላይ የተመላከቱ ጉዳዮች በሚቀርበው የሂሳብ መዝገብ ውስጥ በአግባቡ ማካተቱን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፣ ለዚህ ስራ ያግዘው ዘንድ ከግብር ከፋዩ ሊቀበላቸው የሚገቡ ሰነዶችና መረጃዎችን ለይቶ…

Read More

በተቋሙ ከብልሹ አሰራርና ሌብነት የፀዳ ፍትሃዊ አገልግሎትን መስጠት በየደረጃው ያለ አመራርና ፈፃሚ ተቀዳሚ ኃላፊነት ተገለፀ፡፡

ህዳር 15 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ፣ በሀገር አቀፍ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ ‹‹ትውልድን በስነ ምግባር ተቋም በአሰራር›› በሚል መሪ ቃል የፀረ ሙስና ቀንን በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ቢሮው ለከተማዋ ልማት…

Read More

ቢሮው ለወረዳ ማይክሮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ህዳር 1 ቀን 2018ዓም፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ማይክሮ ቅ/ፅ/ቤት አመራሮች በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ ስልጠና ሰጥቷል። የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው የታክስ ጉዳዮች ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ቢሮው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት በተከታታይነት እያከናወነ ይገኛል…

Read More

በየደረጃው ያለው ፈፃሚ የአገልጋይነት ስብእና በመላበስ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ ፡፡

ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ። በቢሮው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት አዲስ በተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ በየደረጃው ለሚገኘው የሰው ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው ፡፡ በቢሮው የቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተገኝተው እንደገለጹት ስልጠናው ለቢሮው ሰራተኞች በዕውቀት…

Read More

ቢሮው በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስራ መስራቱ ሕጋዊውና ሕገወጡን በቀላሉ መለየት የሚያስችል መሆኑን ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች ገለጹ ፡፡

ነሐሴ 13 / 2017 ዓ / ም የአዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ማድረጉ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከልና የአሰራር ግልጽነት ከመፍጠሩም ባሻገር ሕጋዊውና ሕገወጡን በቀላሉ መለየት የሚያስችል በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመርካቶ በመደብራቸው ሲሰሩ ያገኘናቸው ነጋዴዎች ገለጹ ፡፡ የዝግጅት ክፍላችን በመርካቶ አካባቢ በመዘዋወር ቢሮው ወደ ተግባር ባሸጋገር…

Read More

ቢሮው የቁጥጥር ስርዓቱ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ባርኮድ የተካተተበት የመታወቂያ ካርድ ማዘጋጀቱ ግልፀኝነት የተላበሰ የቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት ያለው ቁርጠኛነት ማሳያ ነው ሲሉ ያነጋገርናቸው የመርካቶ ነጋዴዎች ገለጹ

ነሐሴ 07 / 2017 ዓ / ም የአዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ እያካሄደ የሚገኘውን የቁጥጥር ስራ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ከብልሹ አሰራር ለመከላከል የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን በትላንቱ ዕለት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ በመገኘት የንግዱ ማህበረሰብን ቢሮው ወደ ተግባር ባሸጋገር በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስርዓት ላይ ያላቸውን…

Read More