እስካሁን ግብራቸውን ያልከፈሉ የቤትና የቦታ ግብር ከፋዮች በተቀሩት ቀናት የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ።
የካቲት 11 ቀን 2017 ዓም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በየደረጃው የሚገኘው አመራር እስካሁን ግብራቸውን ያልከፈሉ የቤትና የቦታ ግብር ከፋዮች በተቀሩት ቀናት የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል።
ይህ የተገለፀው በቢሮው የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ የማዕከል ዳይሬክተሮች የቅርንጫፎች ድጋፍ አፈፃፀም በገመገሙበት መድረክ ነው።
ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ እንደገለጹት በየካቲት ወር የተጀመረው የክትትል ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው አመራሩ ታች መርዶ ሲደግፍ እንደገምጋሚ ሳይሆን ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ስራው ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
በቀጣይም የቤትና የቦታ ግብር፣ የደመወዝ ገቢ ግብር፣ የአከራይ ተከራይ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታክስ ኦዲት፣ የደረሰኝ ሕትመት፣ የእዳ ክትትል ፣ የታክስ ቅሬታ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልፅግና!