ቢሮው ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዲስ የታክስ ኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያዎች ስለተቋሙ ተልዕኮ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የinduction ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

ቢሮው ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዲስ የታክስ ኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያዎች ስለተቋሙ ተልዕኮ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የinduction ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አዲስ ወደተቋሙ ለተቀላቀሉ የታክስ ኦዲት አጣሪ ሠራተኞች የኢንዳክሽን ( Induction ) ስልጠና ቢሮው በተቋቋመበትን ዓላማ ፣ ተልዐኮና ተያያዥ የታክስ ኦዲትአጣሪ አሰራር ስርዓቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

ስልጠናውን በይፋ ከፍተው ያስጀመሩት በቢሮው የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ እንደገለፁት ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ የተጣለበትን ገቢ ለመሰብሰብ ከሚተገበሩ ስራዎች አንዱ በአዲስ ወደ ቢሮው ለሚቀላቀሉ ሰራተኞች የኢንዳክሽን ( Induction ) ስልጠና መስጠት ነው ብለዋል ።

ስለሆነም ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል የቢሮውን ዓለማና ተልዕኮ በአግባቡ በመገንዘብ ተቋማዊ ዲስፕሊን በመያዝ ወደ ስራ ሲገቡ የተጣለባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ሃላፊው አስገንዝበዋል ።

በቢሮው የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ጋዲሳ ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች አዋጅ ፣ በሰራተኞች ሙያዊ ስነምግባር ፣ በታክ ኦዲት አሰራርና አተገባበር ፣ በተክስ ኦዲት ውሳኔ ጥራት አሰራርና አተገባበር እንዲሁም በታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዙሪያ መሆኑን ገልፀዋል ።

ስልጠናው በውስጥ አቅም የሚሰጥ ሲሆን ለተከታታይ አራት ቀናቶች የሚሰጥ ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *