ተማዋ ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ አዳዲስ የገቢ ማበልፀጊያ ፕሮጀክቶች መቀረፃቸው ተገለፀ። ።

የከተማዋ ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ አዳዲስ የገቢ ማበልፀጊያ ፕሮጀክቶች መቀረፃቸው ተገለፀ። ።

መጋቢት 9 / 2017 ዓ / ም ፥ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከኤፍ ኤም 96.3 ሬድዮ ጋር ዛሬ በነበረው የቀጥታ ስርጭት ቢሮው የከተማዋ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ የማስቻል ስራዎችን ለመስራት እየተገበራቸው ያሉ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የታክስ አማካሪ ወይዘሮ ሰነይት ፀጋዬ ከጣቢያው ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በቀጣይ ከተማዋ ለምትሰራቸው ሰው ተኮርና ሰው ተኮር ላልሆኑ ስራዎች ከፍተኛ መጠን ያላው ገንዘብ ያስፈልጋታል ይህንንም ለማሳካት የተለያዩ የታክስ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በመቅረፅ ስራዎች እየሰራ ነው ብለዋል ።

የመጀመሪያው ፕሮጀክት ከግብር ከፋዮች ጋር በተያያዘ የንግድ ቤቶች የደመወዝ ገቢ ግብር ፣ የንግድ ቤት አከራይ ተከራይ ግብር ፣ የቅይጥ ንግድ ገቢ ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ግብር ፣ የንግድ ድርጅቶች ደረጃን እና ያለንግድ ፈቃድ ህገወጥ ንግድ የሚነግዱ ነጋዴዎችን በተመለከተ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ የተጀመረ ሲሆን ይህም በጥናቱ መሰረት ወደ ታክስ ስርዓት እንዲገባ ይደረጋል ብለዋል ።

በተጨማሪም በሁለተኛው ፕሮጀክት ግብር ከፋዩ ያለደረሰኝ ገዝቶ በስቶክ ያስቀመጠውን ዕቃ ተቋሙ ባዘጋጀው ቅፅ ላይ ግብር በሚከፍልበት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመሄድና በትክክል በመሙላት በዓመቱ መጨረሻ እንደወጪ እንዲመዘገብላቸው በማድረግ ወጥ የሆነ የግብይት ሰንሰለት እንዲኖር የማስቻል ስራ እየተሰራመሆኑን ገልፀዋል ።

የንግዱ ማህበረሰብ እነዚህ ፕሮጀክቶች በእኔነት ስሜት በመቀበል የሚፈለግባቸውን ማስረጃ ቢሮውን ባዘጋጀው ቅፅ መሰረት ተገቢውንና ትከከለኛ መረጃ በመስጠት ለገቢው መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።

ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *