‹‹በጀግኖች አባቶቻችን ለነፃነታችን ለተከፈለ ዋጋ የሚገባው ክብር እየሰጠን የአርበኞች ቀንን አገልግሎት በመስጠት በስራ በማሳለፋችን በእጅጉ ደስተኞች ነን!›› የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች

‹‹በጀግኖች አባቶቻችን ለነፃነታችን ለተከፈለ ዋጋ የሚገባው ክብር እየሰጠን የአርበኞች ቀንን አገልግሎት በመስጠት በስራ በማሳለፋችን በእጅጉ ደስተኞች ነን!›› የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች

ሚያዚያ 27 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ

የሃገራችን ሕዝቦች በቅኝ ላለመገዛት ያደረጉት ትግል በድል አድራጊነት የተቋጨበት የአርበኞች ቀንን ለግብር ከፋዮች አገልግሎት በመስጠት በስራ ለማክበር በመቻላችን ደስተኞች ነን ሲሉ በአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች አገልግሎት ሲሰጡ ያገኘናቸቀው አምራሮችና ፈፃሚዎች ገለፁ፡፡

በሌላ በኩልም በቅርንጫፍ ቅ/ፅ/ ቤቱ ክፍያ ለመፈፀም የመጡ ግብር ከፋይ ወራዊ ቫት ማሳወቂያ ቀናት ሊጠናቀቀ ጥቂት ቀናት ብቻ በመቅረታቸው ስጋት ውስጥ ለቅጣት ልንዳረግ ነው በሚል ሰግተን የነበረ ቢሆንም ስራችን ሳይበደል በተረጋጋ መልኩ ነበርን ዛሬ አገልግሎት ማግኘታችን ስጋታችንን ቀርርፏል ሲሉ ነው ተናግረዋል፡፡

ወ/ት ሰብለ ተስፋዬ የተባሉት ግብር ከፋይ በዕለቱ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ አገልግሎት እንደሚሰጥ በቴሌግራም ከተላለፈ መልዕክት በመረዳት ወደ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ለወራዊ ቫት ክፍያ መምጣታቸውን ነግረውናል፡፡

ዛሬ ምንም እንኳን ካላንደር የሚዘጋው የአርበኞች ቀን ቢሆን አመራሩና ሰራተኛው የግብር ከፋዮችን ችግር ለመቅረፍ በቀኑ አገልግሎት መስጠታቸው ሌሎች ተቋማት መማሪያ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ አለማየሁ አበራ፣ አልማዝ ታደለ፣ ሂሩት ባሻ የተባሉ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የሽያጭ መሳሪያዎች የስራ ሂደትና ፈፃሚዎች በበኩላቸው የዘመኑ አርበኝነት በትጋት በመስራት ከድህነት መውጣት ነው ብለውናል፡፡

አባቶቻችን ሀገራችን የህይወት፣ የደምና የአጥንት ዋጋ በመክፈል ነፃነቷ የተጠበቀች ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ እኛም ለልጆቻችን የኢኮኖሚ ነፃነቷ የተጠበቀች ሀገር ለማስረከብ የልማት አርበኞች ልንሆን ይገባልም ሲሉ ገልፃዋል፡፡

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት መንግስቱ በበኩላቸው ዛሬ ላይ የከተማችን ነዋሪን በቀጥታ ተጠቃሚ እያደረጉ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ጨምሮ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች በፍጥነት በማጠናቀቅ የታቀደላቸውን ዓላማ ሊያሳኩ የሚችሉ ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል ነው ብለዋል፡፡

ከተማዋ የምታመነጨው ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ ደግሞ ሁሉንም ቀናት በአግባቡ በመጠቀም መሆኑን በማንሳት በአሁኑ ወቅት በቅርንጫፍ ፅ/ቤታቸው ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሌሎች ዝግ የበዓላት ቀናት ጭምር አገልግሎት የመስጠት ባህል እየዳበረ መምጣቱን ነግረውናል፡፡

በዛሬው ዕለትም የግብር አወሳሰን፣ የታክስ ኦዲት፣ የእዳ ክትትል፣ የአይሲቲና መሰል ድጋፍ ሰጪ የስራ ክፍሎች ውስጥ ከሚገኙ ፈፃሚዎች ከ2-3 የሚሆኑ በስራ ላይ ሆነው አገልግሎት አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውንም ገልፀውልናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *