ቢሮው በ2018 በጀት አመት የሌብነትና ብልሹ አሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመቅረፍና የተጠያቂነት አሰራር በማጠናከር የታክስ ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡
ነሐሴ 10 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በዋና መስሪያ ቤቱ ፣ በ17ቱ ቅርንጫፎችና በወረዳ ካሉ ከ 7ሺህ በላይ ከሆኑ አመራሮችና ሰራተኞችጋር በመልካም አስተዳደር፣ በአግልግሎት አሰጣጥና በሌብነትና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ውይይት አካሂዷ፡፡ በውይይቱ የቪዲዮ ገለፃ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ በ2018 በጀት…
