“የምንከፍለው ግብር መልሶ እኛን የበለጠ ተጠቃሚ እያደረገን በመሆኑ ግብራችንን በታማኝነትና በወቅቱ እየከፈልን እንገኛለን”

” የምንከፍለው ግብር መልሶ እኛን የበለጠ ተጠቃሚ እያደረገን በመሆኑ ግብራችንን በታማኝነትና በወቅቱ እየከፈልን እንገኛለን” አቶ ዘርዓይ ዕቁባይ ኤች ፣ ኤች ኢ

ኢንጂነሪንግ ዋና ስራአስኪያጅ ።

ሚያዚያ 25 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ርንፅ ፅ/ቤት ግብር ከፋይ ከሆኑት የኤች፣ ኤች ኢንጂነሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘርዓይ ዕቁባይ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት “ግብር የምንከፍለው ተገደን ሳይሆን የምንከፍለው ግብር ፣ መልሶ በልማቱ እኛኑ የበለጠ ተጠቃሚና ውጤታማ እንድንሆን ስላደረገን ነው ብለዋል ።

ድርጅታቸው በተሰማራበት የአምራች ፣ ላኪና አስመጪ ዘርፍ መንግስት ባመቻቸው የኢንቨስትመንት ተጠቃሚ ዕድሎች ከቲንሽ ተነስተው እያደጉ በመምጣት ዛሬ ላይ ኤች ፣ ኤች ኢንጂነሪንግ በሀገር ውስጥ የከባድ መኪና ማምረቻ ፣ በኢትዮጵያ የግብርና ውጤት የሆኑ ጥራጥሬና እህሎች ላኪ እንዲሁም ለእንዱስትሪ ግብዐት የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን አስመጪ በመሆን ከተማቸውን ፣ ብሎም ሀገራቸውን በንግዱ አለም በመሠማራት ተጠቃሚና በወቅቱ ማንኛውንም ግብራቸውን በማሳወቅና በመክፈል ታማኝ ግብር ግብር ከፋይ መሆናቸውን በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ሆነው ይናገራሉ ።

በወሩና በአመቱ ግብርን በወቅቱ አሳውቆ በጊዜው ከመክፈል ባሻገር በተጨማሪ የሰራተኞቻቸውን የደመወዝና የጡረታ ግብር በየወሩ ለአፍታ ሳይዘናጉ በትክክለኛ ጊዜ በማሳወቅና በመክፈል ሀላፊነታቸውን እየተወጡና በከተማዋ ልማት ላይ አሻራቸውን በማሳረፋቸውና መልሰው ተጠቃሚ በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን በኩራት ገልፀዋል ።

” የከተማዋ ሁለንተናዊ ልማቶች እጅግ ውብ ፣ ድንቅና ምቹ ሆነው የሚሰሩት ከንግዱ ማህበረሰብ በሚሰበሰብ ገቢ መሆኑን ደጋግመው የሚገልፁት ” አቶ ዘርዓይ ያለፉት 3 ተከታታይ አመታት ድርጅታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታማኝ ግብር ከፋይ በመሆን የፕላቲንየም ደረጃ ተሸላሚ ሲሆኑ ፣ በፌደራል ገቢዎች ደግሞ የሶስተኛ ደረጃ የሲልቨር ተሸላሚ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ይህ መሆኑ ደግሞ ከታማኝነት ግብር ከፋይ የሚመነጨውን የበለጠ ትጋት ፣ ጠንክሮ መስራትና እራሳችንንም ለውጠን ከምናገኘው ገቢ የሚገባንን ግብር አብልጠን እንድንከፍል ትጥቅ ሆኖናል ብለዋል ።

ዋናው ነገር ከምንም በላይ የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ያወጣው የታማኝ ግብር ከፋዮች መለያ የህግ ተገዢነት መስፈርቶችን በሚገባ በሟሟላት ፣ በመፈፀም ፣ ገቢን አሳውቆ በወቅቱና በጊዜው ያላንዳች ችግርና ክፍተት በመክፈል ግዴታንና መብትን የንግዱ ማህበረሰብ እንዲወጣም በአፅንኦት ይገልፃሉ ።

ግብር ከሚሰበስበው ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ( LTO ) የሚደረግላቸው ክትትል ፣ ስልጠና ፣ ድጋፍ፣ ቀልጣፋ አገልግሎትና መልካም ስነምግባር ለስራቸው ትጋት በመሆኑ አመራሮቹንና ሰራተኞቹን ምስጋና በማቅረብ በዚሁ ትጋታቸው እንዲቀጥሉም ያሳስባሉ ።

ግብር መክፈል ከዕድገታችን ጋር የተያያዘ ነው ፤ የምንከፍለው ግብር ከአመት አመት እያደገ ነው ፣ የከተማችንም የመልማትና የማደግ ፍላጎት በመጨመሩ ከአመት አመት የምትሰበስበው ገቢ እያደገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ማንኛውም ከቲንሽ እስከ ትልቅ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ የከተማችን የንግዱ ማህበረሰብ ለዚህ መድረሳችን መንግስት በከፈተልን የኢንቨስትመንት ፣ የንግድ ማበረታቻዎች መሆኑን ላፍታ ልንዘነጋው አይገባም ይላሉ ስራ አስኪያጁ ።

ከግብር ከፋይነት ባሻገር በከተማዋ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ባለን አቅም በመደገፍ ማህበራዊ ሀላፊነታችንን እየተወጣን ነው ያሉት አቶ ዘርዓይ ለዚህም ፋብሪካቸው ባለበት አካባቢ በቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10፤ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የልማቱ አጋር መሆናቸውን ተናግረዋል ፣ ከዚህም ባሻገር በዝቅተኛ ኑሮ ያሉ ወገኖቻችንን በተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች ወቅት በመደገፍም ግዴታቸውን እየተወጡ መሆኑን ነግረውናል ።

በንግድ ዐለም ውስጥ ስላለን ግብር መክፈል ውዴታ ግዴታችን ነው፣ ሀገር ማሳደግ ደግሞ ዳር ቆሞ በመመልከትና በወሬ ስላልሆነ ሁላችንም በተሰማራንበት ለከተማችን ፣ ለሀገራችንና ለመጪው ትውልድ እንስራ ሲሉ መልዕክታቸውን አቶ ዘርዓይ አስተላልፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *