የዚህ ዘመን አርበኝነት የኢኮኖሚ ነፃነቷን ያስከበረች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የራስን አሻራ ማሳረፍ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ቄጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ፈፃሚዎች ተናገሩ፡፡

የዚህ ዘመን አርበኝነት የኢኮኖሚ ነፃነቷን ያስከበረች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የራስን አሻራ ማሳረፍ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ቄጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ፈፃሚዎች ተናገሩ፡፡

ሚያዚያ 27 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ

ጀግኖች አባቶቻችን በምንም የማይተካውን ህይወታቸውን በመገበር ፣ አጥንታቸውን በመከስከስና ደማቸውን በማፍሰስ ነፃነቷ የተጠበቅ ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ እኛም የዚህ ዘመን አርበኝነት የሚጠይቀውን መስዋዕትነት በአግባቡ በመረዳት የተሻለች ሀገር ለልጆቻችን ማስረከብ አለብን ሲሉ የአዲስ አበባ ቄጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ፈፃሚዎች ተናገሩ፡፡

የዝግጅት ክፍላችንም በዛሬው ዕለት በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በአካል በመገኘት ለመቃኘት እንደቻለው አብዛኛው የቅርንጫፉ አመራርና ፈፃሚ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በስራ ገበታው በመገኘት አገልግሎት ሲሰጥና ግብር ከፋዮችን ሲያስተናግድ ለመመልከት ችለናል፡፡

በቅርንጫፉ በታክስ ኦዲት የስራ ክትትል ቡድን መሪ ወ/ሮ እታፈራሁ ሰጠኝ የአርበኞች ቀንን አብዛኛው ሰራተኛ በስራ ለማክበር በመቻሉ ተደስቷል ይላሉ፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት በከተማችን ትላልቅ ፕሮጀክቶ እየተጠናቀቁ ለህብረተሰቡ ክፍት መደረጋቸው የሰራተኛውን የስራ ተነሳሽነት በእጅጉ ማሻሻሉ የተናገሩት ቡድን መሪዋ በማስገደድ ሳይሆን በፍላጎት በአርበኞች ቀን በመግባት አገልግሎት መስጠታቸው ለዚህ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የአርበኞችን ቀንን በስራ እንደምናከብር ተገቢው ግንዛቤ አግኝተው አገልግሎቱን በዕለቱ ማግኘት እንዲቻሉ መረጃውን በስልክ በመደወልና በቴሌግራም ጭምር በማስተላለፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው ተደርጓል ሲሉ አስረድተውናል፡፡

በዚህም በዕለቱ የግብር አወሳስን፣ ታክስ ኦዲት፣ ኢንቨስቲጌሽን ኦዲት፣ ዕዳ ክትትል፣ አይሲቲና የመሳሰሉ የስራ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ አብዛኛው ሰራተኛ በመደበኛ የስራ ገበታው በመገኘት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

የቅርንጫፉ ሰራተኛውም በአርበኞች ቀን ብቻም ሳይሆን በላባደሮች ቀን ጭምር በመግባት አገልግሎት መስጠቱን የተናገሩት ወ/ሮ እታፈራሁ የተቋሙን ግብ ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በላቀ የስራ ተነሳሽነት እየሰራ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን አጋርተውናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *