ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት በስራ አፈፃፀም እና በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ከፍተኛ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች ዕውቅና ሽልማት ሰጠ ፡፡

ነሀሴ 19 / 2018 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በጀት ዓመት በቁልፍ ግቦች የስራ አፈጻጸም እና በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲሁም ለገቢ አሰባሰቡ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ዕውቅና ሰጥቷል ፡፡ የዕውቅናና ሽልማት ስነ ስርዓቱ ዓላማም የ2017 ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በተሻለ አፈፃፀም ማሳካት…

Read More

የኢኮኖሚ ነፃነቷን በማረጋገጥ የበለፀገች ሀገር መገንባት የዚህ ትውልድ ተቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የካቲት 09/2018 ዓ.ም የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች 130ኛው የአድዋ ድል ምክንያት በማድረግ ውይይት አካሄዱ፡፡ የአድዋ እሴት ለሁለንተናዊ ሃገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የድል በአል አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ የፅ/ቤት ኃላፊው አቶ አዳነ ሱሌ አድዋ ዘመን የማይሽረው በደማቅ የተጻፈ የድል ታሪክ፣ ጀግኖች አባቶቻችን ድንበር ተሻጋሪና ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ቀንዲል የሆኑበት፣ ለእኛ ኢትዮጲያውን…

Read More

በመዲናዋ በኤሌክትሮኒከስ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በተካሄደ የታክስ ኦፕሬሽን በ6 የንግድ ድርጅ

ታህሳስ 25 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሰራ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን፣ ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 6 ድርጅቶችንና 9 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ። ቢሮው በዛሬው ዕለት መርካቶን ጨምሮ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ…

Read More

በመዲናዋ በተሽከርካሪ ጎማዎች ንግድ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በተካሄደ የታክስ ኦፕሬሽን በ11 የንግድ ድርጅት ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ታህሳስ 11 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተሸከርካሪ ጎማ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ባካሄደው የኦፕሬሽን ተግባር ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል፡፡ በዛሬው ዕለት ቢሮው ያካሄደው ድንገተኛ የኦፕሬሽን ተግባር ለረጅም ቀናት በተካሄደ ጥናት ላይ የተመሰረተ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት…

Read More

ቢሮው በማዕከልና በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ለሚገኙ አመራሮች በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ቢሮው በማዕከልና በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ለሚገኙ አመራሮች በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡ ሀምሌ 21 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን ተከትሎ ነው፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው ለማዕከልና ለቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጆችና ምክትል ስራ አስኪያጆች፣ የስራ ሂደት መሪዎች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን…

Read More

በ2018 በጀት አመት ለመሠብሰብ የታቀደውን ገቢ ለማሳካትና የህግ ተገዢነት ስራን ለማጠናከር ወደ 24 የሚጠጉ አሰራሮችን ወደ ተግባር በማሸጋገር ተጨባጭ ውጤቶች እየታዩበት መሆኑ ተገለፀ ።

ነሐሴ 14 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት አመቱ የታቀደውን የከተማዋን ገቢ በአግባቡ ለመሠብሰብ አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተግባር አስገብቶ እየሰራ ይገኛል ። ፍትሀዊ የሆነ የታክስ ( ግብር ) አሰባሰብ ስርዓት በከተማዋ ማስፈንና ይበልጥም የሚሰበሰበው ገቢ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን በህግ ተገዢነት ዘርፍ አሰራርን በመፈተሽ በማስተካከልና…

Read More

በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ በፊት ከሚደርስባቸው ማጭበርበር እንደታደጋቸው በመርካቶ ያነጋገርናቸው ግብር ከፋዮች አሳወቁ ።

ነሐሴ 12 / 2017 ዓ / ም የአዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል ። የኮሙንኬሽን የዝግጅት ክፍላችን በመርካቶ አካባቢ ዛሬም በመዘዋወር ቢሮው ወደ ተግባር ባሸጋገረው በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስርዓት ላይ ያለውን ሂደት የታክስ ( ግብር ) ከፋዮች አስተያየት ቅኝት አድርጓል ፡፡ በመርካቶ…

Read More

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት(AFD) ለገቢዎች ቢሮ በንብረት ታክስ (Property tax) አተገባበር ላይ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ፡፡

መስከረም 26 ቀን 2018ዓ.ም ፣ ገቢዎች ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት ልዑካን ቡድን ጋር በንብረት ታክስ አስተዳደር፣ የትግበራ ሂደትና ድጋፍ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 5 ዓመታት በገቢ ዘርፉ ተጨባጭ ለውጦችን ለማስመዝገብ መቻሉን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡ በዚህም በ2010 ዓ.ም በከተማ አስተዳደደሩ…

Read More

የገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች “በእመርታና ማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ

በዓላትን በጋራ እናክብር” በሚል መሪ ሀሳብ በሚከበሩት የመስቀል/ደመራ እና የእሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄዱ። መስከረም 10 / 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በአደባባይ በሚከበሩት በዐላት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ይዞ እንዲያከብር የሚያስችል የመወያያ ሰነድ በቢሮው የታክስ ኢንተለጀንሲ ዳይሬክተር በአቶ ተስፋዬ ነጋሽ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የመስቀል ደመራና…

Read More

በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ግብአት አከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ በተካሄደ የታክስ ኦፕሬሽን ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 11 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡

ጥር 9 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተከናወነ የተጠና፣ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 11 የኮንስትራክሽ ግብአቶችን በማከፋፈል ንግድ ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ። ቢሮው አርብ ጥር 8 ቀን 2018ዓ.ም መርካቶን…

Read More