በመዲናዋ በ19 ስጋ ቤቶችና በ6 የግንባታ እቃዎች መሸጫ ቤቶች ላይ በተካሄደ ኦፕሬሽን 32 ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ጥር 23 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተከናወነ የተጠና፣ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን በ25 የንግድ ድርጅቶች ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 32 በስጋ ቤትና በግንባታ እቃዎች ንግድ ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ። ቢሮው ቅዳሜ ጥር…
