በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ከ5 ሺህ በላይ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር በመካሄድ ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ ደረሰኝ እንዲቆረጥ መደረጉ ተገለፀ።

ህዳር 17 ቀን፤2018፣ አዲስ አበባ፣ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አራት ወራት በ5 ሺህ 203 የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር ማካሄዱ ተገልፆል፡፡ የደረሰኝ ቁጥጥሩ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ በሚገቡ፣ከከተማዋ በሚወጡና በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ ነው የተካሄደው፡፡ በዚህም ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ…

Read More

ከአዲስ አበባ የሚወጡ እና የሚገቡ እንዲሁም በከተማዋ ወደተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጫኑት ዕቃ ህጋዊ ደረሰኝ እንዲቆርጡ የሚካሄድ ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

ነሀሴ 25/ 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ወደ ከተማዋ የሚገቡና የሚወጡ እንዲሁም በከተማዋ ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጫኑት ጭነት ህጋዊ ደረሰኝ ስለመያዛቸው ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። የቁጥጥሩን ስራ ሲያስተባብሩ የነበሩት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የታክስ መረጃና የሽያጭ መመዝገቢያ አስተዳደር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለማየሁ አበራ የቁጥጥሩ ዋና…

Read More

የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ልዑካን ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለመዘርጋት እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

መስከረም 10/ 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቢሮው በመገኘት ቢሮው የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ቀልጣፋ ፣ ውጤታማ ፣ ከሙስና የፀዳ እና ግቡን ያሳካ እንዲሆን የዘረጋቸው አሰራሮች እና ስትራቴጂዎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ለቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ…

Read More

የቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍና የቢሮ ፅ/ቤት በጋራ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎቹን አስቀመጠ ።

ጥቅምት 5 / 2018 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቢሮው የሞደርናይዜሽንና የፅ/ቤት ዘርፍ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት አቅዶ ያከናወናቸውን ቁልፍ እና አበይት ተግባራት አፈፃፀሙን ገምግሟል ። የግምገማውን መድረክ የመሩት የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ አብዱረማንና የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ ናቸው። በውይይት መድረኩም በዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ፣…

Read More

የቁጥጥር ባለሙያዎች ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለመዘርጋት ቢሮው የሚያደርገው ጥረት እንዲሳካ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የተጠናከረ የሕግ ማስከበርና የቁጥጥር ስራ ፍትሃዊነት ላይ በማተኮር የሚተገበር መሆኑን ነው በዛሬው ዕለት ከቁጥጥር ሰራተኞች ውይይት በተካሄደበት ወቅት የተገለፀው። በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በ2017 በጀት አመት ከገቢ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው ገልፀዋል። በበጀት ዓመቱ ለተመዘገው ውጤትም በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ፈጻሚ ተቀናጅቶ መስራት ከፍተኛ…

Read More

በመዲናዋ በሱፍ ልብስ ንግድ ስራ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የካቲት 15 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተከናወነ የተጠና፣ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን በ5 የሱፍ ልብስ ንግድ ድርጅቶች ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 7 ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ። ቢሮው የካቲት 14 ቀን 2018ዓ.ም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች…

Read More

ለግንዛቤዎት

የግብር ከፋዩን የሂሳብ መዝገብ የሚያዘጋጁ የሂሳብ አዋቂዎች እና የውጪ ኦዲተሮች ኃላፊነት እና ሚና • የሂሳብ ባለሙያው የግብር ከፋዩ አመታዊ ግብር ለማሳወቅም ሆነ ለመደበኛ የኦዲት ስራ የሚያዘጋጀው የሂሳብ መዝገብ በቢሮው በተዘጋጀው የአሰራር ሰነድ ላይ የተመላከቱ ጉዳዮች በሚቀርበው የሂሳብ መዝገብ ውስጥ በአግባቡ ማካተቱን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፣ ለዚህ ስራ ያግዘው ዘንድ ከግብር ከፋዩ ሊቀበላቸው የሚገቡ ሰነዶችና መረጃዎችን ለይቶ…

Read More

በሞደርናይዜሽን ዘርፍ ወደተግባር በተሸጋገሩ አሰራሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በሞደርናይዜሽን ዘርፍ ወደተግባር በተሸጋገሩ አሰራሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የታቀደ የ256 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት 24 የሚደርሱ አሰራሮች ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል። ቢሮው በየደረጃው የሚገኙ የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ እና ተጠሪነታቸው ለጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑ አመራሮች እንደሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ በተሻሻሉ 3 አሰራሮች ዙሪያ…

Read More

ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የ2 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ ወር የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀመጠ፡፡

መስከረም 07 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት አመት የታክስ ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ፣ ከሌብነት ፣ ብልሹ አሰራሮችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመላቀቅ ገቢን በላቀ ደረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ 24 የሚደርሱ አሰራሮች በመዘርጋት ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል ፡፡ በዛሬው ዕለትም ከቅርንጫፎችና ወረዳዎች ጋር ባካሄደው የግምገማ መድረክ የበጀት ዓመቱ የ2…

Read More

በመዲናዋ በ19 ስጋ ቤቶችና በ6 የግንባታ እቃዎች መሸጫ ቤቶች ላይ በተካሄደ ኦፕሬሽን 32 ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ጥር 23 ቀን 2018ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሀዊነት ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተከናወነ የተጠና፣ የተቀናጀና ድንገተኛ ኦፕሬሽን በ25 የንግድ ድርጅቶች ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 32 በስጋ ቤትና በግንባታ እቃዎች ንግድ ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ። ቢሮው ቅዳሜ ጥር…

Read More