በደንበኞች ለታክስ ኦዲት የሚቀርቡ ሰነዶች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በሶፍት ኮፒ በማደራጀት ማቅረባቸው የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ለማቀላጠፍና የሰነዶች ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ ነው ሲሉ የኦዲት ባለሙያዎች ገለፁ፡፡

በደንበኞች ለታክስ ኦዲት የሚቀርቡ ሰነዶች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በሶፍት ኮፒ በማደራጀት ማቅረባቸው የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ለማቀላጠፍና የሰነዶች ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ ነው ሲሉ የኦዲት ባለሙያዎች ገለፁ፡፡
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለመዘርጋት የታቀደው የደንበኞች የታክስ ኦዲት ሰነዶች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በሶፍት ኮፒ በተደራጅተው እንዲቀርቡ የሚያስችል አሰራር ስርዓት የአገልግሎት አሰጣጡን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ የሰነዶች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው ሲሉ የከፍተኛና የመካከለኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ባለሙያዎች ገለፁ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ እንዲሁም የህግ ማስከበር ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ በአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችና የአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በመገኘት ባለሙያዎችን ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡
በቅርንጫፍ ፅ/ቤታቸው እስካሁን ሲተገበር የቆየው የወረቀት አሰራርም ከብዛታቸው አኳያ ለደንበኞችም ለማጓጓዝ አዳጋች ለኦዲተሩም አልፎ አልፎ ከቆይታ ብዛት በአይን በመመልከት ትክክለኛነታቸውን ለማረጋገጥ አዳጋች እያደረገባቸው እንደሚገኝ ነው ባለሙያዎቹ ተናገሩት፡፡
ይሁንና ደንበኞች ለታክስ ኦዲት የሚያቀርቧቸውን ፋይሎች ያይጠራቀም በፊት ስካን በማድረግ በሶፍት ኮፒ ከስር ከስሩ በማደራጀት በኦዲት ወቅት በሶፍት ኮፒ የሚያቀርቡበት ስርዓት ቢዘረጋ በርካታ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚረዳ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
አሰራሮችን በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ ማዘመን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ሁሉ ውስን ችግሮች ሊያጋጥሙ ቢችሉም ችግሮቹን እየተከታተሉ ለማረምና የተመረጡ አጠራጣሪ ሰነዶችን ለማጣራት የአርድ ኮፒ አሰራርን ጎን ለጎን ጠቃሚው የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና