የቢሮው አመራሮች የአዲስ አበባ ከፍተኛና የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

የቢሮው አመራሮች የአዲስ አበባ ከፍተኛና የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
ወቅቱ የግብር መክፈያ ወቅት እንደመሆኑ መጠን የገቢ ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቹ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
ጥቅምት 07 /2017 ዓ/ም ፤ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የአዲስ አበባ ከፍተኛና የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
በዛሬው ዕለት በቅርንጫፍ ፅ./ቤቶቹ በመገኘት ጉብኝት ያካሄዱት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ እንዲሁም የህግ ተገዢነት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ ናቸው፡፡
በጉብኝቱ ወቅትም አቶ ቢኒያም ምክሩ ወቅቱ የግብር መክፈያ ወቅት እንደመሆኑ መጠን ክፍተኛና መካከለኛ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ዝቅግት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር በከፍተኛና በመካከለኛ ግብር ከፋዮች የሰው ኃይል አጠቃቀም ፣ ከቢሮ አደረጃጀትና ከወረቀት ሰነድ የኦዲት አተገባበርና ችግሮች እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚስዋሉ ክፍተቶች ለማረም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቹ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *