ቢሮው ,ከታክስ ኦዲት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍቶችና ብልሹ ድርጊቶች ለመከላከል ሪፎርም በማድረግ የታክስ ኢዲት ጥራት አረጋጋጭ የስራ ክፍል አደራጅቶ ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ተገለፀ፡፡ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ቢሮው ,ከታክስ ኦዲት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍቶችና ብልሹ ድርጊቶች ለመከላከል ሪፎርም በማድረግ የታክስ ኢዲት ጥራት አረጋጋጭ የስራ ክፍል አደራጅቶ ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ተገለፀ፡፡
ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከታክስ ኦዲት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍቶችና ብልሹ ድርጊቶች ለመከላከል የሚያስችል የታክስ ኢዲት ጥራት አረጋጋጭ የስራ ክፍል በማደራጀት ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ተገለፀ፡፡
በቢሮው የታክስ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ ሰናይት ፀጋዬ የታክስ ኦዲት ጥራት አረጋጋጭ የስራ ክፍልና አሰራር ከተቋሙ በሚወጡ የታክስ ውሳኔዎች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና አተገባበር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚረዳ ነው፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም ከቢሮው የሚወጡ የታክስ ውሳኔዎች እና ቢሮውን እየተጠቀመባቸው ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አተገባበር ዙሪያ የሚሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች ለማረምም ይረዳል ብለዋል፡፡
አዲሱ አደረጃጀትና አሰራር ለተገልጋዮች የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት በበጀት ዓመቱ የታቀደውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡
የታክስ ኦዲት ጥራት የማረጋጋጥ ኃላፊነት የተሰጠው ይህው የስራ ክፍል ከቢሮው የሚወጡ የኦዲት ውሳኔዎች አሰራራቸው በታክስ ህግ መሰረት ትክክልኝነትን ማረጋገጥና ሌሎች ኃላፊነቶች ተሰጥተውት የተደራጀ መሆኑም አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የታቀደ ገቢ በውጤታማነት ለማሰባሰብ እንቅፋት የሆኑ የአሰራርና የአደረጃጀት ክፍተቶች በመለየት ለማረም የሚያስችል ተቋማዊ ሪፎርሞች በማካሄድ የታክስ ኦዲት ጥራት አረጋገጋጭና የእዳ ክትትል የስራ ክፍሎችን በማደራጀት ወደ ተግባር ማስገባቱ ይታወቃል።
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልጽግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *