ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በብልሹ አራሮችና በሌብነት ድርጊቶች ውስጥ ገብተው ባገኛቸው 2 አመራሮችና 34 ፈፃሚዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ፡፡

ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በብልሹ አራሮችና በሌብነት ድርጊቶች ውስጥ ገብተው ባገኛቸው 2 አመራሮችና 34 ፈፃሚዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ፡፡
ጥቅምት 9/ 2017 ዓ.ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በብልሹ አሰራሮችና በሌብነት ድርጊቶች ውስጥ ገብተው ባገኛቸው የተቋሙ 2 አመራሮችና 34 ፈፃሚዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ፡፡
በቢሮው የስነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ ቀናው ታከለ ከዝግጅት ክፍላቸን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ቢሮው በበጀት ዓመቱ የብልሹ አሰራርና የሌብነት ማክሰሚያ ዕቅድ በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው አመራሮች ፣ ፈፃሚዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ የጋራ በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ይሁንና በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሩብ ዓመት በተደረገ ክትትል በብልሹ አሰራሮችና የሌብነት ድርጊቶች ውስጥ ገብተው በተገኙ በ26 ሰራተኞች ላይ የቀላልና በ10 ሰራተኞች ላይ የከባድ የዲስፒሊን ቅጣት ተወስዷል ብለዋል
ከባድ ቅጣት ከተጣለባቸው ውስጥ 2 አመራሮች ሲሆኑ አሰራሮችን በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሲሆን 2ቱ የቡድን አስተባባሪዎች እና 6ቱ ፈፃሚዎች በቀጥተኛ ከብልሹ አሰራርና ከሌብነት ጋር መሆኑን ገልፀው በፈፃሚዎቹ ላይ የደመወዝ ቅጣት እና ከደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሰሩ የተደረጉ መሆኑን ሃላፊው ገልፀው ።
በቀጣይ የሚቀርቡ ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ የማጣራት እና ወደ ዲሲፕሊን የሚላኩ ጉዳዬችን በመላክ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መታገል ለአንድ ክፍል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም አመራር ፣ ፈፃሚና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ! ለአዲስ አበባ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *