በመዲናዋ በደረሰኝ ቁጥጥር የህግ ተገዢነትን ለማስፈን የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለፀ።
ታህሳስ 15/ 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96.3 ሬድዮ ጋር ” ገቢ ለአዲስ ” የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም በታክስ ህግ ተገዢነት ፣ በደረሰኝ ፣ በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማዳበር የሚያስችል ውይይት አካሂዷል ።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው መርሀ ግብር በቢሮው የታክስ ኢንተለጀንሲና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እና የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር አዲሱ በነበራቸው የቀጥታ ስርጭት ቆይታ እንደገለፁት ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግብራቸውን ህግን መሠረት ባደረገ መልኩ እንዲከፍሉ ደረሰኝ ፣ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም እና የሂሳብ መዝገብ መያዝ እንዳለባቸው ገልፀዋል ፡፡
የታክስ ግዴታዎችን ባልተወጡ የግብር ከፋይ ማህበረሰብ የሚወሰዱ እርምጃዎችእና መፍትሔዎችን አመላካች ውይይት አካሂደዋል ።
የእጅ በእጅ ደረሰኝ፣ የሀሰተኛ ደረሰኝ የመከላከልና የህግ ተጠያቂነት ማድረግ ዙሪያ አንስተዋል ።
ተጠያቂ ለማድረግ የኦፕሬሽን ስራዎች መሠራታቸውንና በፖሊስ በኩል ለአቃቤ ህግ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል
የቅሬታ አቀራረብ በተመለከተ በደረሰኝም ሆነ በማንኛውም አገልግሎት አሰጣጥ በየደረጃው ግልፅ አሰራር መኖሩን ሀላፊዎቹ አንስተዋል ።
በታክስ አስተዳደሩ ላይ የሚሰሩ ወንጀሎችና የሚያደርሱ ጉዳቶችን ሁሉም አካላት በጋራ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባ ተመላክቷል ።
የታክስ ህግ ግዴታቸውን ባልተወጡ ግብር ከፋዮች ቢሮው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችንና አሰራሮችን ከማስፈን ባሻገር በየደረጃው ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል
ግብር ከፋዮች ግንዛቤ እንዲያድግ በርካታ ስራዎች መሠራቱን የግንዛቤ ስልጠና፣ ቤት ለቤት ክትትልና ድጋፍ ፣ ገፅ ለገፅ ግንኙነት በመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ።
ግብር ከፋዩ የሚሰጣቸውን ትምህርትና ግንዛቤ ይጠቅመኛል ብሎ መከታተልና ወደ ውጤት መለወጥ እንደሚገባም ሀላፊዎቹ አመላክተዋል ።
ለነጋዴው ሆነ ለግብር ከፋዩ ማሽንም ሆነ ትክክለኛ ደረሰኝ እንዲኖራቸው የሚደረገው ትክክለኛ ግብራቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉ ለማድረግ መሆኑ በውይይቱ በአፅንኦት አንስተዋል ።
ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች አለመጠቀምና አለመመዝገብ ፣ ያለደረሰኝ ወይም ሀሰተኛ ደረሰኝ መጠቀም ነው ያሉት ሀላፊዎቹ
በሀሰተኛ ማንነት መመዝገብ፣ አድራሻ ማጥፋት ፣ ሀሰተኛ ደረሰኞች ማተምና መጠቀም እነዚህ ተግባሮች በህግ ተይዘው በህግ ውሳኔ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ተገልፆል ።
በመጨረሻም ግብር ከፋዩ ( የንግዱ ማህበረሰብ) ከወንጀልና ከፍትሀ ብሔር ተጠያቂነት ለመዳን ራሳቸውን መጠበቅ ፣
ትክክለኛ ደረሰኝ በመጠቀም የመንግስትን ገቢ መክፈል እንዳለበት ተጠቁሟል
#ውጤታማ_የገቢ_አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልጽግና !
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
ድረ ገጽ፦ www.aarevenuesbureau.gov.et
ቴሌግራም፦ https://t.me/aarevenues
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Addis Ababa Revenue Bureaue
ፋና ቴሌቪዥን እሁድ ማታ ከ1፡30 ዜና በኋላ፣
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ሰኞ ማታ ከ3፡00 ዜና በኋላ፣
አዲስ ሚዲያ ኤፍ ኤም ሬድዮ 96.3 ማክሰኞ ከ5:00 – 6:00፣
ገቢያችን ህልውናችን ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 7075 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን መጠየቅ ወይንም ማግኘት ይችላሉ፡፡