የቢሮውን ተልዕኮ በአግባቡ የተረዳና የጋራ ዓላማ ለማሳካት በቁርጠኛነት የሚተጋ አመራርና ፈፃሚ መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
============================
ታህሳስ 14 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በየሳምቱ ሰኞ ማለዳ ‹‹ አብሮነት ለለውጥ›› በሚል መሪ ሃሳብ የሚያካሂደው መድረክ በተቋሙ የጋራ መናበብ ያለውና ተቋማዊ ተልኮውን በአግባቡ የተረዳ አመራርና ፈፃሚ ለመገንባት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በዛሬው እለት የቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱቃድር በአብሮነት መድረኩ ‹‹ አብሮነት ለለውጥ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
በተቋሙ የተጀመረው የአብሮነት መድረክም ለአንድ ዓላማ የተሰባሰበ አመራርና ፈፃሚ ይበልጥ እንዲግባባ፣ ተልዕኮውን በመረዳዳትና በመግባባት እንዲወጣ በማስቻል የተቋሙን አገልግሎቶችን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ለማጎልበት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና!
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
ድረ ገጽ፦ www.aarevenuesbureau.gov.et
ቴሌግራም፦ https://t.me/aarevenues
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Addis Ababa Revenue Bureaue
ፋና ቴሌቪዥን እሁድ ማታ ከ1፡30 ዜና በኋላ፣
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ሰኞ ማታ ከ3፡00 ዜና በኋላ፣
አዲስ ሚዲያ ኤፍ ኤም ሬድዮ 96.3 ማክሰኞ ከ5:00 – 6:00፣
ገቢ ለአዲስ ዲጂታል ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 7075 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን መጠየቅ ወይንም ማግኘት ይችላሉ፡፡