የቢሮው የወርቃማ ሰኞ <<የአብሮነት >> መድረክ ተጠናክሮ ቀጥሏል በቢሮው የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ልምዱን አካፍሏል ።
ሀምሌ 22 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በቢሮው የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ እሙዬ አደራ በዘርፉ ሰፊ የስራ ልምዳቸውን ፣ ተግዳሮቶችን በመልካም ምላሽ የፈቱበትን መንገድና ኦዲት ችግር ከመከሰቱ በፊት ችግሮችን አቃላይ መሆኑን በማጣቀሻ እያመሳከሩ አቅርበዋል
ሙያው ቅንነት ፣ ትህትናንና መረጃና ማስረጃን መሠረት አድርጎ የሚከወን ተግባር በመሆኑ በስራው ዘርፍ ያላችው ወጣቶች ይህንን መርህጨልትከተሉ ይገባል ሲሉ መክረዋል ።
የቢሮው የሰኞ ወርቃማ ቀን የርስ በርስ የልምድ ልውውጥ ፣ መቀራረብና የዕውቀት ሽግግር ተጠናክሮ በመቀጠሉ ፣ ሰራተኞችም ዕውቀትና ልምድ እያገኙበት መሆኑን ጭምር ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል ።