ተቋሙ የከተማዋን ገቢ አልቆ ለመሠብሰብና የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ ለማስፈፀም የቅንጅታዊ የተቋማት አሠራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ ።

ተቋሙ የከተማዋን ገቢ አልቆ ለመሠብሰብና የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ ለማስፈፀም የቅንጅታዊ የተቋማት አሠራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ ።

መስከረም 06 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ቢሮው በ2017 የበጀት አመት ዕቅድ ዙሪያ የተቋማትና የባለድርሻ አካላት የቅንጅታዊ ስራዎች ውይይትና የፊርማ ስነስርዓት አካሄደ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የበጀት ዐመቱ ያቀደውን የላቀ ገቢ አሰባሰብ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር የሚያከናወናቸውን ተግባራት ዙሪያ በጥልቀ በመወያየት በዕቅዶች ዙሪያ የስራ ስምምነት ፊርማ አካሂዷል ።

የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ ለማድረግ በበጀት አመቱ የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ውል ከ25 ከሚሆኑ የፌደራል ፣ የክልል ከተሞች እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት አመራሮችና ተወካዮች ጋር በ12 ወራት የቢሮውና የቅንጅታዊ ትስስር የፈጠሩ ተቋማት ዕቅድ ሰነድ ቀርቦ በቤቱ ውይይት በማድረግ በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች አቅጣጫዎችን በማመላከት ተካሂዷል ።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እንደ ተቋምና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅትና ተቀራርቦ በመስራት በበጀት አመቱ እንደ ከተማ የታቀደው 230.4 ቢሊየን ብር ገቢ ውጤታማ እንዲሆነ በቅንጅት ከተቋሙ ጋር ገቢ የሚሰበስቡ ተቋማት በጋራ በዕቅዶች ላይ ተግባብተን እንዲሰበስቡ የጣለባቸውን ዕቅድ እንዲያሳኩ የስምምነት ፊርማውና ውይይቱ ወሳኝ ነው ብለዋል ።

አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ቀልጣፋ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ተደራሽ እና ፍትሓዊ እንዲሆን በማድረግ የደንበኞችን እርካታ በመጨመር ከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዐመቱ ያቀደውን ገቢ መሠብሰብ ይገባልም ሲል አሳስበዋል ።

የቢሮው አማካሪ አቶ ዮሴፍ ግርማ በበኩላቸው ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ የስራ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ከገባ በኃላ የሚጠበቀውን ገቢ ለመሠብሠብ በበላይነት በቢሮው እንደሚመራ እና ውጤቱንም በከተማ ደረጃ እየተገመገመ እንዲሁም የታዩ ክፍተቶች በቀጣይ እንዲስተካከል በጥብቅ በመምራትና በመሥራት የታቀደውን ገቢ ለማሳካት የባለድርሻ አካላት የውይይትና የግምገማ መድረክ ወሳኝ እንደሆነም አመላክተዋል

በመድረኩ የተገኙት ባለድርሻ አካላት የቢሮውን ተነሳሽነትና ሪፖርት አቀራረብ በማድነቅ በ2017 በጀት ዐመት ከተማዋ የምታመነጨውን ኢኮኖሚ በአግባቡና በወቅቱ ለመሠብሰብ እንዲቻል ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጠንካራና ክፍተቶቾ በመግለፅ የበጀት አመቱ ገቢ አሰባሰብ እንዲሳካ እንደተቋማቸው ሚናቸውን በሚገባ እንደሚወጡ አፅንኦት በመሥጠት ተናግረዋል ።

በገቢ አሰባሰቡ ከተቋሙ ጋር ሊኖር የሚገባውን የመረጃ ልውውጥ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ የስነ ምግባር ግድፈቶችን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ፣ የተቋም ግንባታ አፈፃፀሞችን በሚገባ ለመፈፀም ፣ የታክስ ህግ ተገዢነት ለማስፈን እንዲሁም ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሠብ ያስችል ዘንድ የበኩላቸውን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርጉና በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል

የ2017 የበጀት አመቱ የቢሮውንና የቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ መነሻ የመወያያና የመግባቢያ ሰነድ በቢሮው የለውጥ ስራዎች ቡድን ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ ጌታሁን ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል ፡፡

በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ፣ ሀሳቦችና አስተያየቶች በቢሮው አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል

በመድረኩም ከቢሮው ጋር የስራ ስምምነት ፊርማ በመፈራረም ለቅንጅታዊ ስራ ወደ ተግባር የገቡት ተቋማት የፌደራልና የከ ተማ አስተዳደር ተቋማቶች ሲሆኑ ከእነርሱም አዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ፣ ንግድ ቢሮ ፣ ቤቶች ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ፣ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፣ የፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር ፣ የአዲስ አበባ ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን፣ ኢትዮ ቴሌከም ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ፣ ኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ፣ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ሌሎችም ተቋማት ተገኝተዋል ፡፡

#ውጤታማ_የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *