ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማሰባሰብ የዕቅዱን 86 በመቶ ማሳካቱ ተገለፀ፡፡ ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው፡፡

ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማሰባሰብ የዕቅዱን 86 በመቶ ማሳካቱ ተገለፀ፡፡
ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው፡፡
ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም፥ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 54 ነጥብ 92 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ 47 ነጥብ 24 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ የእቅዱን 86 በመቶ ማሳካቱ ተገለፀ፡፡
በዛሬው ዕለት ቢሮው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ እቅድ አፈፃፀም ላይ ከከፍተኛና መካከለኛ ግብር ከፋዮች እንዲሁም ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ቢሮው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሰባሰበው ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ37 ነጥብ 65 በመቶ ወይም የ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑ ነው የተናገሩት፡፡
የተመዘገበው የገቢ አፈፃፀም ከባለፈው ዓመት አንፃር በ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ቢሆንም ከዕቅድ አኳያ ሲመዘን በ14 በመቶ ዝቅ ያለ በመሆኑ አመራሩ በቀጣይ ክፍተቱን ለመሙላት በሚያስችል ደረጃ ተግባራቱን መምራት እንደሚገባውም ተናግረዋል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ መሰብሰብ አቅሙን ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ የገቢ አቅሞችን በመለየት ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ መደረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በገቢ ዘርፉ የሚስተዋሉ የሌብነትና ብልሹ አሰራሮች ለመከላከልም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የታክስ ኢዲት ጥራት የሚያረጋግጥና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን እንዲሁም የታክስ ዕዳ ክትትል የሚያደርጉ አደረጃጀቶች በጥናት ተለይተው ወደ ተግባር ማሸጋገራቸው ተናግረዋል፡፡
የተጠያቂነት አሰራር ከማስፈን አኳያም ብልሹ አሰራሮችና የሌብነት ድርጊቶች ውስጥ ገብተው የተገኙ አመራሮችና ባለሙያዎችን በህግ ተጠያቂ የማድረግ እርምጃዎችም መወሰዳቸውንም አመላክተዋል፡፡
በመድረኩ የቢሮው የዕቅድና በጀት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ግርማ የቢሮውን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልጽግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *