ቢሮው የንግድ ፈቃድ ለማደስ የግብር ግዴታቸውን ለተወጡና መሟላት የሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎችን ላሟሉ ግብር ከፋዮች ፈጣን የክሊራንስ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ገለፀ ፡፡

ቢሮው የንግድ ፈቃድ ለማደስ የግብር ግዴታቸውን ለተወጡና መሟላት የሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎችን ላሟሉ ግብር ከፋዮች ፈጣን የክሊራንስ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ገለፀ ፡፡
ታህሳስ 11 ቀን 2017ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓመታዊ የንግድ ፈቃድ ያለቅጣት ለማደስ የሚጠበቅባቸውን የግብር ዕዳ በመክፈል ክሊራንስ ለሚጠይቁ የንግዱ ማህበረሰብ የተሳለጠ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑ ገለፀ ፡፡
በቢሮው የስታንደርዳይዜሽን ዝግጅት አገልግሎት አሰጣጥ፣ድጋፍና ክትትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ወይንሸት ጸጋዬ የበጀት ዓመቱ የንግድ ፈቃድ ያለቅጣት ማደሻ ወቅት እስከ 30 / 2017 ዓ . ም መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የግብር ግዴታቸውን ለተወጡ ነጋዴዎች ለንግድ ፈቃድ ዕድሳት የሚያስፈልገውን ማስረጃ ( ክሊራንስ አገልግሎት ) በተሳለጠ መልኩ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም የሚጠበቅባቸው የግብር ግዴታ ያልተወጡና የግብር ዕዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች የክሊራንስ አገልግሎት እንደማይሰጥ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ግብር ከፋዮች የክሊራንስ አገልግሎት ለማግኘት አስቀድመው ግብራቸውን መክፈል እንደሚጠበቅባቸው አሳውቀዋል፡፡
ከከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ የንግድ ፈቃድ ወስደዉ በመስራት ላይ ያሉና የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ነጋዴዎች መኖራቸውን የገለፁት ወይዘሮ ወይንሸት በቀሪዎቹ የንግድ ፈቃድ ያለቅጣት ማደሻ ቀናት በመጠቀም የንግድ ፈቃዳቸውን ለማደስ የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል ፡፡
ቢሮው ለንግዱ ማህበረሰብ ቀልጣፋ የክሊራንስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ አሰራሮችን በመዘርጋት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ! ለአዲስ አበባችን ብልፅግና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *