የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ለታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ ።

የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ለታክስ ከፋዩ ሕብረተሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ ።
ታሕሳስ 14 / 2017 ዓ /ም ፥ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
ቢሮው የታክስ ከፋዩ ማህበረሰብ የተሰለጠ አገልግሎት ለመስጠት የአደረጃጀት፣ የአሰራርና ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም የባለሙያው የአመለካከትና የክህሎት ችግሮችን በመፍታት በአገልጋይነት መንፈስ አገልግሎት እንዲሰጡ እያደረገ ይገኛል ።
በዛሬው እለትም የዚህ ሪፎርም ስራ አካል የሆነው ከዋናው መስሪያ ቤትና ከየቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተወጣጡ ባለሙያዎች የደንበኞች አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ኤች ኤስ ቲ ከተባለ የኦዲት፣ የማማከርና ስልጠና ከተባለ ኩባንያ ጋር በመተባበር ስልጠና መስጠት ተጀመረ ።
ስልጠናው ሲሰጡ ያገኘናቸው የኩባንያው ባልደረባ የሆኑት ወይዘሮ መሰረት ተሾመ እንደገለፁት የስልጠናው አላማ ለገቢዎች ቢሮ ሠራተኞች የደንበኞቻቸውን ፍላጎት በአግባቡ ተረድተው የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የሚያደርግና ተነሳሽነትን የሚፈጥር ስልጠና ለመስጠት መሆኑን ጠቅሰዋል ።
ስልጠናው በደንበኞች አያያዝ፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ በተግባቦት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመው ሰልጣኙ በስልጠናው ያገኙትን እውቀት እንደእርሾ በመጠቀም ፣ ያላቸውን እውቀት በማሳደግ ለታክስ ከፋዩን ፍላጎት ያገናዘበ አገልግሎት እንዲሰጡም አሳስበዋል።
ስልጠና በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ መሰረት በስልጠናው የተሳተፉ ስልጠናው መነሻ በማድረግ እኔ የቱ ጋ ያለሁት ክፍተቴ ምንድነው በሚል ውስጣቸውን በመፈተሽና በስልጠናው ያገኙትን ስትራቴጂ በመጠቀም ራሳቸውን ማብቃት እንዳለባቸው ጠቁመዋል ።
በመጨረሻም ቢሮው የሠራተኞችን ክህሎት ለማሳደግ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል ።
# ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልፅግና!
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.aarevenuesbureau.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/aarevenues
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Addis Ababa Revenue Bureaue
📺 ፋና ቴሌቪዥን እሁድ ማታ ከ1፡30 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ሰኞ ማታ ከ3፡00 ዜና በኋላ፣
📻 አዲስ ሚዲያ ኤፍ ኤም ሬድዮ 96.3 ማክሰኞ ከ5:00 – 6:00፣
📑 አዲስ ገቢ ዲጂታል ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 7075 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን መጠየቅ ወይንም ማግኘት ይችላሉ፡፡
<img class="x16dsc37" role="presentation" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:

50

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *