ቢሮው በማዕከልና በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ለሚገኙ አመራሮች በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ቢሮው በማዕከልና በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ለሚገኙ አመራሮች በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ሀምሌ 21 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ገቢዎች ቢሮ

የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን ተከትሎ ነው፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው ለማዕከልና ለቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጆችና ምክትል ስራ አስኪያጆች፣ የስራ ሂደት መሪዎች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በገንዘብ ሚኒስቴር የታካስ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዋስይሁን አባተ የገቢ ግብር አዋጁ የታክስ መሰረቱን በማስፋት የመንግስትን ገቢ አሰባሰብ የማሻሻል፤ የታክስ ፍትሃዊነትን የማረጋገጥ፤ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል የመደገፍ፤ ለታክስ ማጭበርበር ምክንያት የሆኑ አሰራሮችን የማስቀረት እንዲሁም በታክስ ውሳኔ ለክርከር በር የሚከፍቱ አንቀጾችን ግልጽ የማድረግ ዓላማዎች በማንገብ መሻሻሉ ተናግረዋል፡፡

የቀድሞው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ በበርካታ ጉዳዮች የፍትሃዊነት ጥያቄዎች የሚነሱበት ነበር ያሉት አቶ ዋሲይሁን የተሻሻለው አዋጅ አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በማስፋት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አዲሱ አዋጅ በታክስና በሀገራዊ ምርት ዕድገት (Tax to GDP ratio) መካከል ያለውን ሰፊ ክፍተት በማጥበብ እንደሀገር የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጁ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል መደገፍ ዓላማ ያደረገ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ዋሲይሁን የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱ ቀላልና ተገማች የሚያደርግ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ከህግ ተገዢነት አኳያም ታክስን የመሰወርና የማጭበርበር ችግሮች በመሰረታዊነት በመቅረፍ የግብር ከፋዩን የህግ ተገዢነት ለማጎልበት የሚያግዝ ነውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *