ቢሮው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የታክስ ዕዳ አሰባሰብ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር ተግባራዊ ማድረጉ ተገለፀ።

ቢሮው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የታክስ ዕዳ አሰባሰብ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር ተግባራዊ ማድረጉ ተገለፀ።
ጥቅምት 10 / 2017 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የታክስ ዕዳ አሰባሰብ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር ተግባሪያዊ ማድረጉ ተገለፀ።
በቢሮው የታክስ ሂሳቦች አስተዳደር ዳይሬክቶሬ ዳይሬክተር አቶ ታዬ ማስረሻ ለቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ወደ ተግባር የተሸጋገረው አዲሱ አሰራርና አደረጃጀትና ቀደም ሲል የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የታክስ ዕዳ ክትትል ውጤታማነት የሚያጎለብት ነው ብለዋል።
አዲሱ አደረጃጀትና አሰራር ወደ ተግባር መሸጋገር በከተማዋ የታክስ ዕዳ ከአመት አመት እየጨመረ መምጣት ምክንያት መሆኑንም ነግረውናል።
የዕዳ አሰባሰብ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ በመጠቀም መከታተል እንዲቻል፣ የታክስ ዕዳዎች በዕድሜያቸውና በመጠናቸው ተለይተው ክትትል በማድረግ ወደ ገቢ እንዲቀየሩ ለማድረግና የዕዳ አሰባሰብ ሒደቱ ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ፍትሐዊ ለማድረግ ታስቦ መደረጉንም ገልጸዋል።
የታክስ ዕዳ ክትትል አደረጃጀት የፌደራል ገቢዎች ሚንስቴርና አለም አቀፍ ተሞክሮዎች መነሻ በማድረግ በጥናት ተለይቶ ወደተግባር የተሸጋገረ መሆኑንም አስረድተዋል።
መጠናቱን ገልጸዋል።
አዲሱ ዳይሬክቶሬት የታክስ እዳዎችን ከመለየት ጀምሮ እስከ መሸጥ ያለው ስራ የሚሰራ መሆኑን በማውሳት በዋናው መስሪያ ቤት ሁለት ቡድኖች እንደሚኖሩትም ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ 20 ቢሊዮን ብር ያልተሰባሰበ የታክስ ዕዳ በተወሰኑ ግብር ከፉዮች ዘንድ መኖሩ መረጃዎች ያመላክታሉ
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልጽግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *