የቢሮው የ2017 መጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃጸር በ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው ተባለ፡፡

የቢሮው የ2017 መጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃጸር በ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው ተባለ፡፡
ጥቅምት 12 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑ ተገለፀ፡፡
ይህ የተገለጸው በትናንቱ ዕለት የቢሮው የጀነራል ካውንስል አባላት የበጀት ዓመቱን የ3 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሞችን በማቅረብ ውይይት በተካሄደበት መድረክ ነው፡፡
በዚሁ ጊዜ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ቢሮው በጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ47 ቢሊዮነ3 ብር በላይ በመሳባሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ አሳክቷል ብለዋል፡፡
ዕቅድ አፈፃፀሙም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር የ37 በመቶ ወይም የ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ይሁንና በሩብ ዓመቱ ሊሰባሰቡ የሚችሉ ገቢዎችን አሟጦ ማሰባሰብ ቢቻል ኖሮ ዕቅዱን ከዚህም በላይ ማሳካት ይቻል ነበር ያሉት ኃላፊ ለዚህ ይህ በተወሰኑ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ያጋጠሙ በአመራር ክፍተት የተፈጠረ መሆኑም አመልክተዋል፡፡
በቀጣይ ከደረሰኝ ጋር ያሉ የመጭበርበር ችግሮች ለመቅረፍ በተለየ መልኩ አቅዶ መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
ከተጨማሪ ስኬት ታክስ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉና በዜሮና በተመላሽ የሚያስመዘግቡ ግብር ከፋዮችን በመከታተል የመረጃዎች ትክክለኛነት ማረጋገጥ የእንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የቢሮቀውን የአሰራር ስርዓት በቴክኖሎጂ በመደገፍ አሰራሮችን ለማቀላጠፍና ለገቢ አሰባሰብ ውጤታማነት ለማሳደግ በሚያስችል ደረጃ ለማድረስ ወደ ተግባር የተሸጋገሩና በቀጣይ በቅንጅት ለመተግበር የታቀዱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በፍጥነት ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገባልም ብለዋል፡፡
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተመለከተ ወቅታዊ ፣ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን በጥራት ለማግኘት #ትክክለኛውን የማህበራዊ ሚዲያ ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! እናመሠግናለን !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *