በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ የሚካሃድ ግብይት በደረሰኝ ብቻ እንዲፈፀም የሚደረግ ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተገለፀ ።

በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ የሚካሃድ ግብይት በደረሰኝ ብቻ እንዲፈፀም የሚደረግ ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተገለፀ ።
አስመጪ ፣ አከፋፋይ ፣ አምራችና ቸርቻሪዎች የሚገበያዩበት ስርዐት በደረሰኝ ብቻ መሆኑ እንዳለበትም ተመላክቷል
ህዳር 05 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዛሬ በመርካቶ ካሉ የነጋዴ ማህበር ተወካዮች ጋር በደረሰኝ ግብይት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል ።
መድረኩን የመሩት የቢሮው ሀላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ ” በመርካቶም ሆነ በከተማዋ የሚካሄዱ ግብይቶች በደረሰኝ ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን አስቀድሞ መስራቱንና እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል
አስመጪ ፣ አከፋፋይ ፣ አምራችና ቸርቻሪዎች ጋር ያሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት እና መድረኮችን ፈጥሮ በመወያየት ወደ ህጋዊነት ለመግባት አስቻይ ስራዎች መሠራታቸውን የጠቆሙት አቶ ቢንያም ከህዳር 01 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአስመጪ፣ በአከፋፋይ ፣በአምራችና በቸርቻሪ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን አመላክተዋል ።
በመሆኑም በከተማችን በደረሰኝ ብቻ መገበያየት ላይ መንግስትም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ለድርድር የማያቀርበው ጉዳይ እንደሆነ ተገልጿል ።
በደረሰኝ መገበያየት የመንግስት እና የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ አቋም መሆኑን ያብራሩት አቶ ቢንያም በደረሰኝ ለመገበያየት የሚስተዋሉ ችግሮችን ህገወጥ ደላሎች ፣ አጭበርባሪዎችንና ደረሰኝ መስጠት የማይፈልጉ አምራች፣ አስመጪና አከፋፋይን ማጋለጥ ፣ ጥቆማ መስጠትና ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም በጋራ ለለውጥ ልንሰራ ይገባል ብለዋል ።
ስለሆነም በአሁኑ ወቅት አስመጪ፣ አከፋፋይ ፣ አምራችና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት የማይችሉ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው ለዚህም በመርካቶ ለሚደረግ ቁጥጥር አዲስ ሰራተኞች በማደራጀት በ58 ብሎኮች በመመደብ ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመው ፣ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ራሳቸውን ካለደረሰኝ ግብይት ሊጠብቁና በደረሰኝ ግብይት ሊፈፅሙ እንደሚገባ ተገልፆዋል ።
ከተማዋ ከምትሰበስበው ገቢ 63% የሚሆነው በከተማዋ ለሚታዩ ሰው ተኮር ልማትና ሜጋ ፕሮጀክቶች እንደሚውል የተገለፀ ሲሆን ለዚህ ስኬት የንግዱ ማህበረሰብ በደረሰኝ በመግዛትና በመገበያየት ሚናውን ሊወጣና መብቱን ሊያስከብር እንደሚገባ ተገልጿል ።
በውይይቱ የተሳተፉ አንዳንድ አከፋፋይና ቸርቻሪ በንግድ ዘርፉ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ አሉ ያላቸውን ችግሮች በማንሳት ውይይት የተደረገ ሲሆን በደረሰኝ ግብይት መፈፀም ላይ መግባባት ተደርሷል ።
በመሆኑም ቢሮው ለንግዱ ማህበረሰብ የሚያካሂደውን ግብይት በደረሰለኝ ብቻ እንዲመሠረት በድጋሚ በመድረኩ ላይ ጥሪውን አስተላልፉአል ።
#የላቀ_ገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *