ከንቲባ አዳነች ግብር እና ደረሰኝ ከመቁረጥ ጋር በተያያዘ ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ምላሽ:-

ከንቲባ አዳነች ግብር እና ደረሰኝ ከመቁረጥ ጋር በተያያዘ ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ምላሽ:-
በመርካቶ ህጋዊ ግብይት እንዲደረግና ለእያንዳንዱ ግብይት ነጋዴው ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለን:: እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በዘላቂነት ለማስተካከል የምናደርገውን ጥረት በጥናት ላይ ተመርኩዘን ክትትል ስናደርግ የቆየን ሲሆን ያገኘነው ግኝት በርካታ ህገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንዳሉ ተመልክተናል:: በዚህም ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል::
ግብር ለማስከፈል እና ደረሰኝ እንዲቆርጡ ለማድረግ ባደረግነው ሂደት በሀሰት ውዥንብር በመንዛት መጋዘኖችን በመዝጋት በምሽት እቃዎች ሲጫኑ ተመልክተናል:: ይህ ፍፁም ስህተት ሲሆን ግብርን መሰረተ ልማት ለመዘርጋት፣ ከተማችንን ለማስዋብ፣ ተማሪዎችንና አቅመ ደካሞችን ለመመገብ እንዲሁም ሀገር ለመገንባት የምንጠቀምበት በመሆኑ በቀጣይ ህጋዊ ስርዓት በመዘርጋት እና ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *