የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ መስተዳደሮች የገቢ እቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 18/2017ዓም
የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ተቋማት የአራት ወራት የገቢ እና የዋና ዋና ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በዛሬው መድረክ የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች አጠቃላይ የአቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ለተሳታፊዎች ቀረቧል፡፡ በሪፖርቱ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የነበራቸውን ጠንካራ ጎኖች እና በተግባር የታዩ ክፍተቶችን ለመድረኩ አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቀበታ ከሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የቀረቡት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች አበረታች መሆቸውን አመልክተው በቀጣይ የተለጠጠ እቅድ በማቀድ በሙሉ አቅም መስራት አንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም የገቢ መጠንን ለማሳደግ ከታክስ መረብ ወጪ የሆኑትን ወደ መረቡ ማስጋባት እና አዳዲስ ዘርፎችን ወደ ታክስ መረቡ እንዲካታቱ ማድረግ እንደሚገባ ለዚህም በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡