የቢሮው የጀነራል ካውንስል አባላት በ2018 በጀት ዓመት የከተማና የገቢዎች ቢሮ የገቢ ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ደረሰ፡

የቢሮው የጀነራል ካውንስል አባላት በ2018 በጀት ዓመት የከተማና የገቢዎች ቢሮ የገቢ ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ደረሰ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከ17ቱም የገቢዎች ቢሮ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጆችና ም/ስራአስኪያጆች እንዲሁም የማዕከል ዳሬክተሮች ጋር በ2018 የከተማና የገቢዎች ቢሮ የገቢ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ሰኔ 28/2017 በተካሄደው በዚሁ ውይይት ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት የከተማዋን የወጪ ፍላጎት፣ የቢሮው የ2017 የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም እንዲሁም የከተማዋ የኢኮኖሚ አቅምን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ዕቅዱን ማዘጋጀቱ ተገልፆል፡፡

በውይይቱ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በዕቅዱ መነሻ ሁኔታዎች ላይ ከአመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ዕቅዱ በዋናነት የ2017 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም፣ በበጀት ዓመቱ የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም የከተማዋ ኢኮኖሚ ሊያመነጭ የሚችለውን የገቢ አቅምና የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎት ለመመለስ የሚያስፈልግ የወጪ ፍላጎት መነሻ ማድረጉን አብራርተዋል፡፡

ከዘህም በተጨማሪ የ2018 የገቢ ዕቅድ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተነሳ እየታዩ ያሉ ለውጦችና በከተማዋ የኮሪደር ልማት ጨምሮ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሚፈጥሯቸው ዕድሎች ታሳቢ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ከተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች አኳያም በቢሮው ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማጠናከር፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ለመከላከል፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ እንዲሁም አመራሩንና ፈፃሚውን ለማትጋትና ለማበረታታት ወደ ተግባር የሚሸጋገሩ አዳዲስ አሰራሮች፣ የአደረጃጀቶችና የቴክኖሎጂ ልማቶች ተግባራት እቅዱን ለማሳካት በመነሻነት የተወሰዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የቢሮው የ2017 የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም የከተማዋ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳለው የሚያሳይ ነው ያሉት ኃላፊ ገቢ ሰብሳቢ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች ዕቅዱን የራስ በማድረግ ለማሳካት ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባልም ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት 11 ወራት 202 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 194 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ ለማሳካት ተችሏል፡፡

ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ለአዲስ አበባ ብልጽግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *