በሞደርናይዜሽን ዘርፍ ወደተግባር በተሸጋገሩ አሰራሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የታቀደ የ256 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት 24 የሚደርሱ አሰራሮች ወደ ተግባር ማሸጋገሩ ይታወቃል።
ቢሮው በየደረጃው የሚገኙ የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ እና ተጠሪነታቸው ለጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑ አመራሮች እንደሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ በተሻሻሉ 3 አሰራሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አብዱራሕማን መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት ቢሮው ግብር በብቃት የመሰብሰብ ኃላፊነቱን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ አሰራሮችን ዘርግቷል።
የአደረጃጀት ማሻሻያዎችና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመለየት ወደ ተግባር በማሸጋገር ላይ መሆኑንም ገልፀዋል።
አያይዘውም እንደቢሮ ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለመዘርጋትና ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚረዱ 24 የአሰራሮች በመለየት ወደተግባር አሸጋግሯልም ሲሉ ተናግረዋል።
ከሞደርናይዜሽን ዘርፍ አኳያም የክሊራንስ አገልግሎት፣ የሪከርድና ማህደር እና ከቴክኖሎጂን ውጤቶች ከማስተዳደር ጋር በተያያዘ የነበሩ አሰራሮችን ለማስተካከል ጥረት መደረጉን አንስተዋል።
የታክስ ከፋዮች ምዝገባና አገልግሎት ዳይሬክተር ወይዘሮ አስቴር ዘውዴ ገልጸዋል በበኩላቸው የክሊራንስ አገልግሎት የተደረገው የአሰራር ማሻሻያ ለታክስ ከፋዩ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ነው የገለፁት።
ቴክኖሎጂን ከማስተዳደር ጋር በተያያዘ የተዘጋጀው ሰነድ በመረጃ ቴክኖሎጂ ማስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቡድን አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ምህረትአብ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎች ለሰነዱ ግብዓት የሚሆኑና ግልጽ ያልሆኑላቸው አስተያየቶችን አንስተው ከሚመለከታቸው አመራሮች ምላሽ ተሰጥተዋቸዋል።