የ2018 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የህግ ማስከበር ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የ2018 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የህግ ማስከበር ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ሐምሌ 28 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህግ ተገዢነት ዘርፍ በተጠናቀቀው በጀት አመት ለገቢ መሳካት የተሰሩ አዳዲስ የታክስ ህግ ማስከበር አሰራሮችን በማጠናከር በታዩ ክፍተቶች ላይ አቅዶ በመሥራት በበጀት አመቱ የታቀደውን ገቢ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ ።

የቢሮው የህግ ተገዢነት ዘርፍ ከ17ቱ ቅርንጫፎች የዘርፉ ስራ አስኪያጆች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ ስራ ሂደቶች እና ቡድን መሪዎች ጋር በ2018 በጀት አመት ዋና ዋና የዕቅድ አተገባበር ዙሪያ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።

በቢሮው የህግ ተገዢነት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት እውን ለማድረግ ቢሮው የወረዱ የአሰራር ስርዓቶች መመራት ይገባል ብለዋል፡፡

ከአሰራሮች ጋር በተያያዘም በ17ቱም ቅርንጫፎች በዕውቀት እና በተጠያቂነት ባለው መንገድ መስራት እንደሚገባቸውም ሀላፊው በውይይቱ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።

የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድን ለማሳካትም በ2017 በጀት አመት የተሰሩ ህግ ማስከበር ስራዎች ከተቀመጡ ግቦች ውጤታማ ነበሩ ያሉት ኃላፊ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አብራርተዋል ።

ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ በቀጣይም በተጠናቀቀው በጀት ዐመት የነበረውን አፈፃፀም በላቀ ደረጃ ማስቀጠል እንደሚገባም ተመላክቷል ።

የተቋም ግንባታና የሪፎርም አፈፃፀም ስራዎች ፣ብልሹ አሰራርና ሌብነትን መታገል ፣ የታክስ ህግ ግንዛቤን በማጠናከር የሚዲያና የኮሙንኬሽን ተግባራቶች ፣ የ7075 ነፃ የስልክ መስመር የጥቆማና የምላሽ አሰጣጥ የዘርፉ ቁልፍ ተግባራቶች መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል ።

በውይይቱ አስተያየት ሰጪዎች እንደገለፁት የበጀት አመቱ ዕቅድ በቢሮው እና በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ህግን መሠረት በማድረግ ወጥነት ያለው፣ ግልፅ እና ተጠያቂነት ያለበት የክትትልና የቁጥጥር የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ግብር ( ታክስ ) ህጎችን መሠረት በማድረግ ፍትሀዊ የገቢ አሰባሰብን ለማረጋገጥና የታቀደውን የገቢ ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለመፈፀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ።

የበጀት አመቱ ዕቅድ በዋናነት በደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ቁጥጥር ( ማሽን ) ፣ በስጋት ሥራ አመራር እና የግብር ከፋዮች የህግ ተገዢነት ደረጃ ፣ የታክስ ኢንተለጀንሲ ምርመራ የአሰራር ስርዐት እና በህግ ክፍል የሚከናወኑ ተግባራቶችን የአተገባበርና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *