የታክስ ህግን በማስከበርና ግንዛቤን በማላቅ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ እንደሚያሳካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ አስታወቀ ።

የታክስ ህግን በማስከበርና ግንዛቤን በማላቅ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ እንደሚያሳካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ አስታወቀ ።

ሚያዚያ 19 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

“ከግብር ዕዳ ነፃ የሆነ ብሎክ ወይም ቀጠና እንፍጠር!” በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሁሉም ወረዳዎች የታክስ ህግ ማስከበር የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።

በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ያለው ችግር ለመፍታት ህብረተሰቡን ደረሰኝ ጠይቆ የመቀበል ባህሉን ለማሳደግ እንዲቻል ከህብረተሰቡ ጋር ውይይትአካሂዷል ።

የንቅናቄው ዋና ዓላማ በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ያለው ችግር ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የተቀናጀ ስራ በመስራት በክፍለ ከተማው የሚፈፀሙ ህግ ወጥ ተግባራት በጋራ ለመከላከል እንደሆነም ተገልፅዋል

ይበልጥም ስለደረሰኝ ጠቀሜታ እና ሀሰተኛ ደረሰኝ ጉዳት ግንዘቤ በመፍጠር ሸማቹ ህብረተሰብ ደረሰኝን መሰረት ያደረገ የግብይት ባህል ማሳደግ እና ህገ ወጥ ደረሰኝ በመንግስት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በመረዳት የመድረኩ ተሳታፊዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነም ተመላክቷል ።

በሁሉም ወረዳዎች በተፈጠረ መድረክ ላይ በግብር ከፋዩ እና ሸማቹ ህብረተሰብ ዘንድ ስለደረሰኝ አጠቃቀም ያደገ ግንዛቤ ፣ ያደገ ህግ ተገዥነት፣ ያደገ ገቢ አሰባሰብ እና ያደገ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ያመላከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በክፍለ ከተማው በበጀት ዐመቱ 3,047 ቢልየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብር 3,46 ቢልየን ብር ወይም የዕቅዱን 113.4 በመቶ ማከናወን መቻሉም ተገልጽዋል፡፡

የቅርንጫፉ የህግ ተገዢነት ማስከበር ምክትል ስራ አስኪያጅ አሊሚራህ አብደላ አሊሚራህ የንቅናቄ መድረኩን አስመልክተው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት በዋናነት የመነሻ ሃሳብ ተደርጎ የተወሰደዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጪውን የሚሽፍነው ከተማው በሚሰብሰብ ገቢ በመሆኑና የአስተዳደሩ ገቢ ከዓመት ወደ ዓመት እያደገ በመምጣቱ በዚህ መሰረት በክፍለ ከተማው የታቀደው ዕቅድ በላቀ ደረጃ ገቢን አሟጦ ለመሠብሰብ ግንዛቤን ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል

በከተማ አስተዳደሩ ለገቢ ሰብሳቢው ተቋም በበጀት ዐመቱ 140.291 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዲሰበስብ የተሰጠው ሲሆን ቢሮው ገቢውን በላቀ ደረጃ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ተግባር ገብቶአል፡፡

ስለ ደረሰኝ ጠቀሜታ እና ሀሰተኛ ደረሰኝ ጉዳት ግንዘቤ በመፍጠር ሸማቹ ህብረተሰብ ደረሰኝን መሰረት ያደረገ የግብይት ባህል ማሳደግ እና ህገ ወጥ ደረሰኝ በመንግስት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በመረዳት የመድረኩ ተሳታፊዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የማስቻል ስራ በዉይይት መድረኩ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፡፡

በሌላ በኩል ግብር ከፋዩ እና ሸማቹ ህብረተሰብ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎቸን ያነሱ ሲሆን፤ ለጥያቄዎቹም በቂ ምላሽ መስጠት የተቻለ ሲሆን እንዲሁም ቀጣይነት ያለዉ መድረኮችን በተመሳሳይ መልኩ ቢዘጋጅ ህገ ወጥ ደረሰኝ ላይ ያለዉን ክፍተቶች በመለወጥ እድገት ማምጣት ይቻላል በማለት ምክረ ሃሳብ ግብር ከፋዩ እና ሸማቹ ህብረተሰብ አንስተዋል ።

እንዲሁም በመድረኩ ላይ የተገኝ የተለያዩ አካላት ሊሰበሰብ የታቀደውን ገቢ በአግባቡ ለመሠብሰብ ህገወጥነትንና ማጭበርበርን በጋራ ለመታገል የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

#የላቀ_ገቢ ፣ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *