ቢሮው በተመረጡ የስልጠና ርዕሶች በሶስት ዙር ለሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ።

ቢሮው በተመረጡ የስልጠና ርዕሶች በሶስት ዙር ለሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ።

ሚያዚያ 7 / 2016 ዓ.ም ፡ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ በሦስት ዙር በዋና ቢሮ ለሚገኙ ፈፃሚዎችና አመራሮች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡

በቢሮው የሰው ሀብት ስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ጋዲሳ የስልጠናውን ዓላማ አስመልክተው እንደገለፁት ስልጠናው በየደረጃው የሚገኙ ሰራተኞችን የእውቀት ፣ የክህሎት እና አመለካከት ውስንነቶችን በመሙላት ተቀራራቢ የሆነ የመፈጸም አቅም እንዲኖራቸውና የተሳካ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ነው ብለዋል

ሃላፊው አያይዘውም የሰዉ ሀብት ለተቋሙ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ ጊዜውን የዋጀ ስልጠና በመስጠት እና በማብቃት ተቋሙ የተጣለበትን ግዴታ በአግባቡና በተገቢው መንገድ እንዲወጣ ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል ።

በመሆኑም ፈፃሚውና አመራሩ ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ካላቸው ልምድና ክህሎት ጋር በማቀናጀትና በመፈፀም ተቋሙ እንደከተማ የተጣለበትን ገቢ እንዲሰበስብ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም አስገንዝበዋል ።

ስልጠናው በእውቀትና ስራ አመራር ፣ በተቋም ባህል ግንባታ ፣ በተገልጋይ ተኮር አግልግሎት አሰጣጥ ፣ በተግባቦት ክህሎት እና በስሜት ብልህነት በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በቢሮው ዳይሬክተሮች አማካኝነት መሠጠቱ ታውቋል ፡፡

በስልጠናው ከ300 በላይ የሚሆኑ በዋና ቢሮ የሚገኙ አመራርና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ።

#የላቀ_ገቢ ፣ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *