የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እና HST ( ኤች ኤሴት ) የስልጠና ተቋም ግብርን በላቀ ደረጃ ለመሠብሰብ በሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እና HST ( ኤች ኤሴት ) የስልጠና ተቋም ግብርን በላቀ ደረጃ ለመሠብሰብ በሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡

ሚያዚያ 15 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የሁለትዮሽ ስምምነቱ ዋነኛ ዐላማ በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት የተሰጠውና በገቢ ሰብሳቢው ተቋም በሚመራው የከተማዋ ገቢ አሰባሰብ ከጊዜ ወደ ጊዜ በቴክኖሎጂ ፣ በዕውቀት ፣ በአሰራር፣ በሰው ሀይልና በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በማዘመን ከተማዋ የምታመነጨውን ኢኮኖሚ በአግባብ ለመሠብሰብ እንደሆነ የቢሮው የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ውዴ ቴሶ በፊርማ ስምምነቱ ላዬ ገልፀዋል ።

የተቋሙን አመራር ፣ ሰራተኞች ፣ ግብር ከፋዩን ማህበረሰብና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሥጠቱ ገቢያችንን በአግባቡ ለመሠብሰብና ግልፅነትን ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል ።

የHST ድርጅት ጀነራል ማናጀር አቶ ጌቱ ጀማነህ በበኩላቸው በአገር በቀል የዘርፉ ሙሁራኖች የተቋቋመው ድርጅቱ በታክስ ፣ በቢዝነስ ሰርቪስና በሌሎች ዘርፎች የካበተ የስራ ልምድ ፣ ስልጠናዎችና የማማከር ብቃት ዪለው መሆኑን ገልፀው ከከተማው አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጋር ለለውጥና ለውጤት በጋራ ለመሥራት መፈራረማቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል

በከተማዋ የሚገኙ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ ፣ በፍላጎትና አዋጪ በሆነ መንገድ እንዲከፍሉ ከአመራሩ እስከ ታች ሰራተኛው በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሉ የስልጠናና የአቅም ግንባታ ፓኬጆችን ከቢሮው ነባራዊ ሁናታ ጋር በተዛመደ ያካተተ የሴስራ ውል ስምምነት ፊርማ ተካሂዷል ።

ይህንንም ስምምነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ውዴ ቴሶ ከ HST ተቋም ጀነራል ማናጀር ከአቶ ጌቱ ጀማነህ ጋር ተፈራርመዋል ።

#የላቀ_ገቢ ፣ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *