ቢሮው የ2017 በጀት አመት እቅድን ለማሳካት ከዘርፍ ኃላፊዎችና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ጋር የዕቅድ ስራ ስምምነት ተፈራረመ
መስከረም 04 / 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዐመት ለከተማዋ የሚያስፈልገውን የላቀ ገቢ ለመሰብሰብና እቅዱን ለማሳካት ሚናው የላቀ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮው ሀላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ ይህንንም ለማሳካት ከቢሮው የዘርፍ ሀላፊዎችና ከ16ስቱ ገቢ ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች ጋር የስራ ስምምነት የዕቅድ የፊርማ ስነስርዐት አካሂደዋል ።
በቢሮው የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ፣ የታክስ ጉዳዮች እና የህግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች እንዲሁም የ16ስቱ ገቢ ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች ከቢሮ ሀላፊ ከአቶ ቢንያም ምክሩ ጋር የስራ ዕቅድ የፊርማ ስነስርዓት ያካሄዱ ሲሆን አመራሮቹ ለዕቅዱ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት እንደሚያስፈፅሙም ተመላክቷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት አመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በከተማ አስተዳደሩ የተያዘውን 230 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በብቃት ለመሰብሰብ ያቀደ መሆኑ ታውቋል ።
እንደ ቢሮ ከስሩ ባሉ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ለመሠብሰብ የታቀደው 156.21 ቢሊዮን ብር ሲሆን ይህ ወደ ተግባር ለመለወጥ ነው የስራ ስምምነት ፊርማው የተካሄደው ።
#ውጤታማ _የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !