ቢሮው በ5 ወራት ውስጥ 504,500 ብር በኤች. አይ . ቪ / ኤድስ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ ።

ቢሮው በ5 ወራት ውስጥ 504,500 ብር በኤች. አይ . ቪ / ኤድስ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ ።
ታህሳስ 9/ 2017ዓ0ም : አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በኤች. አይ. ቪ / ኤድስ ምክንያት ለማህበራዊና ለኢኮኖሚው ችግር ለተጋለጡ በቢሮው እና ከቢሮው ውጭ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ገልፆአል
ይህም የተጠቆመው በዛሬው ዕለት ቢሮው በአለም አቀፍ ለ37ኛ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤች. አይ . ቪ / ኤድስ ቀን ከቢሮው ሰራተኞች ጋር እያከበረ ባለበት ነው ።
በቢሮው የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ስርፀትና ማካተት ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ አስቴር ተሰማ የበዓሉን ዓላማ እንደገለፁት ዕለቱን ስናከብር በዚህ በሽታ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡትን ህፃናት ፣ በበሽታው ታማሚ የሆኑ ወገኖችን እንዲሁም በበሽታው ህይወታቸው ያለፋትን ወገኖች ለማሰብ እና በቀጣይ እኛስ ከኤች. አይ . ቪ / ኤድስ ራሳችንና ወገኖቻችንን እንዴት መጠበቅ እንደሚገባን ለማስገንዘብ ነው ብለዋል ።
ስልጠናው ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የሚኒስትሪሚንግ ቡድን መሪ በአቶ ወንድሙ ደንቡ የተሰጠ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በበሽታው የተጠቁ እንደ ሀገር 605 ሺህ እንደ አዲስ አበባ 109 ሺህ ሰዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል ።
ሠራተኛውና አመራሩ 4ቱን የመ ” መርህዎችና የባህሪ ለውጥ በማምጣት እራሱንና ቤተሰቦቹን በመጠበቅ የተጣለበትን ሀገራዊ ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባው አቶ ወንድሙ ገልፀዋል ።
የዘንድሮው የኤች. አይ . ቪ / ኤድስ ቀን ” ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች. አይ .ቪ አገልግሎት ለሁሉም ! “
< TAKE THE RIGHTS PATH > በሚል መሪ ቃል ተከብሯል ።
#ውጤታማ_የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባችን ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *