ቢሮው የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ በአቅም ግንባታ ዙሪያ ከኒዘርላንድ የታክስ ጉዳዮች አማካሪ ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ቢሮው የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ በአቅም ግንባታ ዙሪያ ከኒዘርላንድ የታክስ ጉዳዮች አማካሪ ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
ታህሳስ 9 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ ፣ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አይ ቢ ኤፍ ዲ (IBFD)ከተሰኘ የኔዘርላንድ ዓለም አቅም የታክስ ነክ ጉዳዮች አማካሪ ጋር የከተማዋን ገቢ በላቀ ደረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል አቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
በዛሬው ዕለት በተካሄደው በዚሁ ውይይት የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እድገት እና ለውጥ እያስመዘገበባት የምትገኝ ከተማ እንደመሆኗ መጠን የከተማዋ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በላቀ ደረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት መጨበጥ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቢሮው በዘንድሮ ዓመት ለመሰብሰብ ያቀደው የ230 ቢሊዮን ብር ዕቅድ በተሟላ ደረጃ ለማሳካትም ባለሙያዎች ከዘመኑ ጋር የሚሄድ እውቀት እንዲጨብጡ ማስቻል ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ኃላፊ ቢሮው ከኔዘርላንዱ ለትርፍ ካልተቋቋመ ድርጅት ጋር በስልጠናና በአቅም ግንባታ ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋለ፡፡
የአይ ቢ ኤፍ ዲ( IBFD) ጀነራል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ዶ/ር ቫን ኩመር በበኩላቸው ድርጅታቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጋር ዘመኑ ከደረሰበት የታክስ ፖሊሲና አስተዳደር ፅንሰ ሃሳቦችና አተገባበራቸው ጋር ልምድ ለመለዋወጥና በአቅም ግንባታ ተግባራት በመሳተፍ በጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል፡፡
#ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ፣ለአዲስ አበባ ብልፅግና!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *