የቢሮው የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ የ2016 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከዘርፉ ዳይሬክቶሬቶች፣ ከቅርንጫፎች አመራርና ሰራተኞች ጋር ገመገመ ።

የቢሮው የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ዘርፍ የ2016 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከዘርፉ ዳይሬክቶሬቶች፣ ከቅርንጫፎች አመራርና ሰራተኞች ጋር ገመገመ ።

ሚያዚያ 09 / 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሐላፊ ወ/ሮ ውዴ ቴሶ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በገቢ አሰባሰብ ሂደት ለዘርፉ የተሠጠው ተልዕኮ በታቀዱ ዕቅዶች መሠረት በተገቢው መንገድ ስለመፈጸሙ በመገምገም የታዩ ጠንካራ ጎኖች ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በመለየት በቀሪ ወራቶች ለማረም እና የእርስ በርስ ተሞክሮ ለመውሰድ መሆኑን ገልጸዋል

ባለፋት ዘጠኝ ወራት የዘርፉ አመራሮችና ፈጻሚዎች በቢሮው የትኩረት መሥኮች በተሻለ መነሳሳት ወደ ስራ መግባታቸውን፣ በየደረጃው የግንኙነት ጊዜ በማስቀመጥ ስራዎቻቸው እየተገመገመ መምጣቱ እንዲሁም ሀብትን በቁጠባ ለመጠቀም፣ የስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር፣ ከሰው ተኮር ስራዎች ፣የፈጻሚዎችን አቅም ከመገንባት፣ የላቀ አገልግሎት ከመስጠትና አገልግሎቶችን ከማዘመን ፣ ብልሹ አመራሮችን ታግሎ ከማስተካከል አንጻር አፈጻጸሙ ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ ልዩነት ቢኖረውም ባጠቃላይ የተሻለ አፈጻጸም እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

የዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በ9 ወራቱ የሚመሰገን እንደነበር የገለጹት ኃላፊዋ የሚሠጡ ተልእኮዎችን በተቀመጠው ጊዜና በጥራት በመፈጸም፣ ደንበኞቻችን / ግብር ከፋዮችን በአገልጋይነት ስሜት በማገልገልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዳይፈጠሩ በማድረግ ቢሮው የላቀ ገቢ ለመሰብሰብ ያስቀመጠውን ግብ እንዲሳካ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ በመጠቆም ቀጣይም በቀሪ ወራት ስራቸውን በቁርጠኝነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በመድረኩ የዘርፉን የዋናው መስሪያ ቤት የ9 ወራት ጥቅል ሪፖርት አፈፃፀም በቢሮው የደንበኞች መስተንግዶና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወይዘሮ አስቴር ዘውዴ አማካይነት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የቀረበዉ ሪፖርት መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዋናው መስሪያ ቤት ድጋፍና የእርስ በርስ ጠንካራ ግንኙነት የተሻለ እንደነበር በውይይት ወቅት አንስተዋል ፡፡

በቀጣይ ቀሪ ወራት የሰራተኞች አቅም መገንባት ፣ ተገልጋይን በቅንነትና በፍቅር ማገልገል ፣ ብልሹ አሠራርንና ሌብነትን የሚፀየፍ ፈፃሚ መፍጠር ፣ንብረቶችን በአግባቡ መጠቀም ፣ ቴክኖሎጂን የመጠቀምን አቅም ይበልጥ ማሳደግ ፣ የታቀደውን ገቢ 100++ ማሳካት የትኩረት አቅጣጫዎች ሆነዋል ።

#የላቀ_ገቢ ፣ ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *